በአብዩ አረጋሽ
ከታንዛንያው ክለብ ወደ አትዮጵያ የተመለሰችው የፊት መስመር ተጨዋቿ አረጋሽ ካልሳ ማረፊያ ታውቋል

የኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ ውጤት የሆነችው እና ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እንዲሁም ለመቻል ተጫውታ ያሳለፈችው የፊት መስመር ተጨዋቿ አረጋሽ ኳልሳ በ2017 ዓ.ም ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ወደ ታንዛንያው ያንግ አፍሪካ አምርታ ሁለት ጥሩ የውድድር ዓመታት ካሳለፈች በኋላ ወደ ሀገር ቤት በመመለስ ባለፈው ውድድር ዓመት በሊጉ 2 ኛ ሆኖ ያጠናቀቀውን ኢትዮ ኤልክትሪክ ለመቀላቀል ከስምምነት ደርሳለች።

