በአብዩ አረጋሽ
ዛሬ በተደረጉ የ2019 የውድድር ዓመት የመክፈቻ ጨዋታዎች አዳማ ከተማ ኢትዮ ኤሌክትሪክን ሲያሸንፍ እጅግ ባማረ ድባብ የተካሄደው የበርበሬዎቹ እና ቢጫዎቹ ጨዋታ በአቻ ውጤት ተጠናቀቀ

ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከ አዳማ ከተማ
የሊጉ መክፈቻ በነበረው ጨዋታ በ29′ ደቂቃ አካሉ አቲሞ በአቡበከር ሳኔ ላይ በሰራው ጥፋት የተገኘውን ፍፁም ቅጣት ምት ቢንያም አይተን ወደ ግብነት በመቀየር አዳማ ከተማን መሪ ማድረግ ችሏል ። በአጋማሹ ኢትዮ ኤሌክትሪክ በኩል አብዱልመጅድ ሁሴን 31′ ደቂቃ ላይ በግሩም ሁኔታ ሞክሯት ግብ ጠባቂው አላዛር ማርቆስ ያዳናት ኳስም ቡድኑን አቻ ለማድረግ ተቃርባ ነበር።

በሁለተኛው አጋማሽ በአዳማ ከተማ በኩል አህመድ ሁሴን የግብ ጠባቂውን አልዮንዜ ናፍያንን መውጣት ተመልክቶ ከመሀል ሜዳ የሞከራት ኳስ ተጠቃሽ ስትሄን በኢትዮ ኤልክትሪክ በኩል ለግብ የቀረበ ሙከራ ሳይደረግ ጨዋታው በአዳማ ከተማ 1ለ 0 በሆነ ውጤት መጠናቀቅ ችላል ።
ሀላባ ከተማ ከ ወልዋሎ ዓ/ዩ
10:00 ሰዓት ላይ እጅግ ደማቅ በሆነ ድባብ በሀላባ ስታድየም በተደረገው ጨዋታ በሀላባ ከተማ በኩል ዮናታን ሃይሉ ከፍፁም ቅጣት ምት ክልል ውጪ አክርሮ የሞከረው እና ግብ ጠባቂው አማር ፋል የመለሰውን ሙከራ እንዲሁም ፍሬው ሰለሞን ወደ ፍፁም ቅጣት ምት ክልል አሻምቶት ነፃነት ገብረመድህን ከመስመር ያወጣው ክስተት ሲጠቀስ በወልዋሎ በኩል ሰመረ ሀፍታይ ከጌቱ ሀይለማርያም የተሻገረለትን ኳስ ሳይጠቀምበት የቀረውን እና ካርሎስ ዳምጠው የግቡ አግዳሚ የመለሰበት አጋጣሚ ይጠቀሳሉ ።

በሁለተኛው አጋማሽ በ48′ ደቂቃ ላይ ያሬድ መሃመድ ከቆመ ኳስ አሻምቶት ሽመክት ጉግሳ በግንባሩ ገጭቶ ወደ ግብነት በመቀየር በርበሬዎቹን ቀዳሚ ማድረግ ችሏል። መደበኛው ደቂቃ ተጠናቆ በተጨመረው 6 ደቂቃ ግን ከማዕዘን ምት የተገኘውን ኳስ ሳንባ ሴክ ከግብ ክልሉ ለማራቅ ጥረት ሲያደርግ በእጁ በመንካቱ የተሰጠውን ፍፁም ቅጣት ምት ካርሎስ ዳምጠው ወደ ግብነት በመቀየር ወልዋሎች አቻ እንዲሆኑ አድርጓል ። ጨዋታውም ሀላባ በሽመክት ጉግሳ ግብ እንዲሁም ወልዋሎ በካርሎስ ዳምጠው ግብ 1 ለ 1 በሆነ ውጤት መጠናቀቅ ችሏል ።

