ነብሮቹ ረዳት አሰልጣኝ ሾሙ

ነብሮቹ ረዳት አሰልጣኝ ሾሙ

አሰልጣኝ ሳምሶም አየለ ረዳት አሰልጣኛቸውን ይፋ አድርገዋል

በአዲሱ የውድድር ዓመት በተሻለ ደረጃ ለማጠናቀቅ አሰልጣኝ ሳምሶን አየለን አዲስ አሰልጣኝ አድርገው በመቅጠር የነባር ተጫዋቾቻቸውን ውል በማራዘም እና አዳዲስ ተጫዋቾችን ወደ ስብስባቸው የቀላቀሉት ነብሮቹ ያለ ረዳት አሰልጣኝ ቅድመ ዝግጅታቸውን ሲያከናውኑ መቆየታቸው ይታወሳል።

አሁን ግን ዋና አሰልጣኝ ሳምሶም አየለ ታደሰ ጥላሁንን አብረዋቸው እንዲሰሩ በረዳት አሰልጣኝነት ወደ ስብስባቸው ማካተታቸው ታውቋል። ረዳት አሰልጣኙ ከዚህ ቀደም በቅዱስ ጊዮርጊስ ታዳጊ ቡድን እንዲሁም በዋናው ቡድን ረዳት አሰልጣኝነት እና በአዲስ አበባ ከተማ በተጨማሪም ከሌሎች ክለቦች ዋና አሰልጣኝ በመሆን ሰርተዋል።