በካፍ ቻምፒየንስ ሊግ ሁለተኛው ዙር ጨዋታውን ከሲዳማ ቡና ጋር የሚያደርገው የሱዳኑ አልሂላል ላቀረበው ጥያቄ ምላሽ መሰጠቱን አውቀናል።

ኢትዮጵያን በአፍሪካ ሻምፕዮንስ ሊግ እየወከለ የሚገኘው የወቅቱ የሊጉ ቻምፒየን ሲዳማ ቡና በመጀመሪያው ዙር ማጣሪያ የቻዱን ክለብ ኤግሎንስን በድምር ውጤት 3ለ0 በማሸነፍ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፉ ይታወሳል።
ክለቡ ሁለተኛው ዙር ማጣሪያ ጨዋታውን በቀጣይ ሳምንት እሁድ ጥቅምት 8 በሜዳው ድሬዳዋ ስታዲየም ለማድረግ ቀኑን እየተጠባበቀ ባለበት ወቅት የሱዳኑ ክለብ አል ሂላል “በኢትዮጵያ ባለው ወቅታዊ ሁኔታ የድህንነት ስጋት አለብኝ” ብሎ ያቀረበውን ጉዳይ አስመልክቶ ማብራሪያ ይስጠኝ ብሎ ላቀረበው ጥያቄ ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በኩል ለካፍ በደብዳቤ ምላሽ መሰጠቱን አውቀናል።
ፌዴሬሽኑ በምላሹ ኢትዮጵያ በባህር ዳር ከተማ ከሴኔጋል ጋር ያደረገችውን ትልቁን የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ጨዋታ ያለምንም የፀጥታ ስጋት መካሄዱን ጠቅሶ ከደህንነት ጋር ተያይዞ የሚያሰጋ ነገር እንደሌለ ለካፍ ምላሽ መሰጠቱን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

