የዓለም አቀፉ የስፖርት ገላጋይ ፍርድቤት (ካስ) የካፍን ውሳኔ ሽሮ የሴኔጋልን የአፍሪካ ዋንጫ አሸናፊነት አጸና።

በሞሮኮ አስተናጋጅነት በተካሄደው የ2025 የአፍሪካ ዋንጫ ሴኔጋል ሞሮኮን 1ለ0 አሸንፋ የዋንጫው አሸናፊ መሆኗ ይታወሳል።
በዚህ ጨዋታ ላይ ሴኔጋሎች በጨዋታ መሃል የዳኝነት በደል ደርሶብናል በሚል ጨዋታውን አቋርጠው ወጥተው በድጋሚ በብዙ ውይይቶች ተመልሰው ጨዋታውን መጨረስ ችለው ነበር።
ሆኖም በዚህ ድርጊታቸው ደስተኛ ያልሆነው የአፍሪካ እግርኳስ ኮንፌዴሬሽን ( ካፍ ) ዋንጫው ከሴኔጋል ተነጥቆ ለሞሮኮ እንዲሰጥ ወስኖ ነበር።
ለዓለም አቀፉ የስፖርት ገላጋይ ፍርድቤት (CAS) ይግባኝ የጠየቀችው ሴኔጋልም ጥያቄዋ በብዙ ሂደቶች ካለፈ በኋላ ዛሬ ዋንጫው ተመልሶ እንዲሰጣት ተወስኖላታል።

