የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ከተጀመረበት 1990 ጀምሮ እስካሁን ድረስ 53 ክለቦች ተሳትፈዋል፡፡ ለቀጣዩ የውድድር ዘመን ወደ ፕሪሚየር ሊጉ መግባታቸውን ያረጋገጡት ሸገር ከተማ እና ነገሌ አርሲ በታሪክ 54 እና 55ኛ የፕሪሚየር ሊግ ክለቦች ለመሆን በቅተዋል።
ሶከር ኢትዮጵያም ለግንዛቤ ይረዳ ዘንድ ከ1990 ጀምሮ የተሳተፉ ክለቦች ፣ የመጡበት ዓመት እና የወረዱባቸው ዓመታት እንዲህ አቅርባቸዋለች፡፡
1990
1 ኢትዮ ኤሌክትሪክ * (በ2010 እና 2015 ወርዷል)
2 ኢትዮጵያ መድን * (በ1996 ፣ 2002 እና 2006 ወርዷል)
3 ኢትዮጵያ ቡና * (እስካሁን አልወረደም)
4 ሀዋሳ ከተማ * (እስካሁን አልወረደም)
5 ድሬዳዋ ጨርቃ ጨርቅ (በ1991 ወርዷል)
6 ጉና ንግድ (በ1994 ፣ 1998 እና 2000 ወርዷል)
7 ኮምቦልቻ ጨጨ (በ1991 እና 1993 ወርዷል)
8 ፐልፕ እና ወረቀት (በ1990 ወርዷል)
1991
9 ቅዱስ ጊዮርጊስ * (እስካሁን አልወረደም)
10 ሙገር ሲሚንቶ (በ2007 ወርዷል)
11 ምድር ባቡር (በ1995 ወርዷል)
1992
12 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ * (በ2009 ወርዷል)
13 አዳማ ከተማ * (በ2005 ወርዷል)
14 ትራንስ ኢትዮጵያ (በ2003 ወርዷል)
1994
15 ሐረር ከነማ (1994 ወርዷል)
16 ወንጂ ስኳር (1994 እና 1998 ወርዷል)
1995
17 ኒያላ (በ1996 ፣ 2001 እና 2003 ወርዷል)
18 አርባምንጭ ጨርቃ ጨርቅ (በ1997 ወርዷል)
1996
19 ሐረር ቢራ (ሐረር ሲቲ) (በ2005 ወርዷል)
20 ብርሃንና ሰላም (በ1995 ወርዷል)
1997
21 መቻል * (በ2011 ወርዷል)
22 መተሃራ ስኳር (በ2002 ወርዷል)
1998
23 ንብ (በ2000 እና 2004 ወርዷል)
1999
24 ጥቁር ዓባይ (በ2000 ወርዷል)
25 ሻሸመኔ ከተማ (በ2000 እና 2016 ወርዷል)
2000
26 ደቡብ ፖሊስ (በ2002 እና 2011 ወርዷል)
27 ፋሲል ከነማ * (በ2000 ወርዷል)
28 ውሃ ስፖርት (በ2000 እና 2005 ወርዷል)
29 አዲስ አበባ ፖሊስ (በ2000 ወርዷል)
30 ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ (በ2000 ወርዷል)
31 እህል ንግድ (በ2000 ወርዷል)
32 ኦሜድላ (በ2000 ወርዷል)
2001
33 ድሬዳዋ ከተማ * (በ2004 ወርዷል)
34 ሰበታ ከተማ (በ2002 እና 2014 ወርዷል)
2002
35 ደደቢት (በ2011 ወርዷል)
36 ሲዳማ ቡና * (እስካሁን አልወረደም)
37 ሜታ ቢራ (በ2002 ወርዷል)
2003
38 ፊንጫ ስኳር (በ2003 ወርዷል)
2004
39 አርባምንጭ ከተማ * (2010 እና 2015 ወርዷል)
2006
40 ዳሽን ቢራ (በ2008 ወርዷል)
41 ወላይታ ድቻ * (እስካሁን አልወረደም)
2007
42 ወልዲያ (በ2007 እና 2010 ወርዷል)
2008
43 ሀዲያ ሆሳዕና * (በ2008 ወርዷል)
2009
44 ጅማ አባ ቡና (በ2009 ወርዷል)
45 አአ ከተማ (በ2009 እና 2014 ወርዷል)
2010
46 ወልዋሎ ዓ/ዩ * (እስካሁን አልወረደም)
47 መቐለ 70 እንደርታ * (እስካሁን አልወረደም)
48 ጅማ አባ ጅፋር (በ2014 ወርዷል)
2011
49 ባህር ዳር ከተማ * (እስካሁን አልወረደም)
50 ስሑል ሽረ * (እስካሁን አልወረደም)
2012
51 ወልቂጤ ከተማ (በ2017 ወርዷል)
2015
52 ለገጣፎ (በ2015 ወርዷል)
2016
53 ሀምበርቾ (በ2016 ወርዷል)
2018
54 ሸገር ከተማ
55 ነጌሌ አርሲ
* ምልክት ያላቸው ዘንድሮ እየተሳተፉ የሚገኙ ክለቦች ናቸው።