👉 “የዛሬው ጨዋታ ሽንፈት እኛን አይገልፀንም” – አሰልጣኝ ዘሪሁን ሸንገታ
👉 “በእንቅስቃሴ ረገድ ብዙም ባያስደስትም ግን ማሸነፍ ችለናል” – አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ
ፈረሰኞቹ በአማኑኤል ኤርቦ ብቸኛ ግብ ኢትዮ ኤሌክትሪክን 1-0 በሆነ ውጤት አሸንፈው ሦስተኛ ተከታታይ ድላቸውን ካስመዘገቡበት ጨዋታ በኋላ የሁለቱም ቡድኖች አሰልጣኞች ተከታዩን አስተያየት ሰጥተዋል።
አሰልጣኝ ዘሪሁን ሸንገታ – ኢትዮ ኤሌክትሪክ
“የዛሬው ጨዋታ ሽንፈት እኛን አይገልፀንም። ከእስካሁኑ በተለየ ዛሬ የቀረብንበት አቀራረብ የተሻለ ነበር ነገር ግን ግብ አለመማስቆጠራችን እንድንሸነፍ አድርጎናል።”
አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ – ቅዱስ ጊዮርጊስ
“በእንቅስቃሴው ደስተኛ ባንሆንም የሚያስፈልገን ማሸነፉ ስለነበር እሱን አሳክተናል። ጫና እየበረታብን ሲመጣ መከላከሉን አጠናክረን ሶስት ነጥብ ይዘን ለመውጣት ሞክረናል።።”