ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከ ሀዋሳ ከተማ – ቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1-0 ሀዋሳ ከተማ
70′ ሲሳይ ቶሊ

ተጠናቀቀ!!!!
ጨዋታው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አሸናፊነት ተጠናቀቀ፡፡

90′ መደበኛው የጨዋታ ክፍለጊዜ ተጠናቆ 3 ደቂቃ ተጨምሯል፡፡

85′ የሁለተኛው አጋማሽ ከመጀመርያው በተለየ መልኩ አሰልቺ እና የግብ ሙከራዎች የሌሉበት ሆኗል፡፡ በርካታ የሃይል አጨዋወቶችም እየተስተዋሉ ይገኛሉ፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ሀዋሳ
72′ ሙሉጌታ ምህረት እና ጋዲሳ መብራቴ ወጥተው አስጨናቂ ሉቃስ እና በረከት ይስሃቅ ገብተዋል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ባንክ
71′ ግቡን ያስቆጠረው ሲሳይ ቶሊ ወጥዦ አብዱልከሪም ሃሰን ገብቷል፡፡

ጎልልል!!!! ባንክ
70′ ሲሳይ ቶሊ ባንክን ቀዳሚ ያደረገች ግብ ከመረብ አሳርፏል፡፡

68′ ኤፍሬም አሻሞ ያሻገረውን ኳስ ሰለሞን ገብረመድህን ሞክሮ ለጥቂት ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ባንክ
59′ ታዲዮስ ወልዴ ወጥቶ አምሃ በለጠ ገብቷል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ሀዋሳ
56′
ታፈሰ ሰለሞን ወጥቶ ዮሃንስ ሰገቦ ገብቷል፡፡

ተጀመረ!!!
2ኛው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለጊዜ ተጀምሯል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ባንክ
ዳንኤል አድሃኖም ወጥቶ አዲሱ ሰይፉ ገብቷል፡፡

እረፍት!!
የመጀመሪያው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ካለ ግብ ተጠናቋል፡፡

45′ መደበኛው 45 ደቂቃ ተጠናቆ 1 ደቂቃ ተጨምሯል፡፡

39′ ግርማ በቀለ የመታው ቅጣት ምት በግቡ አናት ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡

33′ ታፈሰ ሰለሞን ግማሽ ጨረቃ ውስጥ የተመቻቸ ኳስ አግኝቶ የመታው ኳስ በግቡ አናት ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡

30′ አስቻለው ግርማ ከመድህኔ የተሻገረለትን ኳስ በቀጥታ መትቶ ለጥቂት ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡

28′ ፊሊፕ ዳውዚ ከፍፁም ቅጣት ምት ክልል የቀኝ ጠርዝ የመታው ኳስ ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡

21′ ኤፍሬም አሻሞ ከግብ ክልሉ የቀኝ መስመር አክርሮ የመታው ኳስ የግቡን ቋሚ ለትሞ ተመልሷል፡፡

17′ ፊሊፕ ዳውዚ የግብ ክልሉን ለቆ የወጣው ቶቤጎ አናት ላይ የሰደደው ኳስ የግቡን አግዳሚ ገጭቶ ተመልሷል፡፡

15′ ጨዋታው የተቀዛቀዘና በመሃል ሜዳ እንቅስቃሴ የተገደበ ሆኗል፡፡

7′ ኤፍሬም ዘካሪያስ ከርቀት የመታውን ኳስ ፌቮ በቀላሉ ይዞታል፡፡

*** ኢማኑኤል ፌቮ የሙሉጌታ ምህረትን የፍፁም ቅጣት ምት አድኖታል፡፡

የፍፁም ቅጣት ምት
4′
ቢንያም ሲራጅ በመዳህኔ ላይ በሰራው ጥፋት ለሀዋሳ የፍጹም ቅጣት ምት ተሰጥቷል፡፡ ቢንያም ሲራጅ የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡

ተጀመረ!
ጨዋታው በንግድ ባንክ አማካኝነት ተጀምሯል፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አሰላለፍ

1 ኢማኑኤል ፌቮ
98 ዳንኤል አድሃኖም – 16 ቢንያም ሲራጅ – 5 ቶክ ጀምስ – 27 አንተነህ ገብረክርስቶስ
4 ጋብሬል አህመድ – 18 ታዲዮስ ወልዴ

21 ኤፍሬም አሻሞ – 8 ሰለሞን ገብረመድህን – 19 ሲሳይ ቶሊ

9 ፊሊፕ ዳውዚ

ተጠባባቂዎች
64 ዳዊት አሰፋ
11 አብዱልከሪም ሀሰን
17 ስንታለም ተሻገር
15 አዲሱ ሰይፉ
6 አምሃ በለጠ
4 ሳሙኤል ዮሃንስ
10 ዳኛቸው በቀለ

የሀዋሳ ከተማ አሰላለፍ
1 ብርያን ቴቤጎ

7 ዳንኤል ደርቤ – 8 ግርማ በቀለ – 17 ሙጂብ ቃሲም – 12 ደስታ ዮሐንስ

3 ኤፍሬም ዘካርያስ – 21ሙሉጌታ ምህረት

13 አስቻለው ግርማ – 5 ታፈሰ ሰሎሞን – 11 ጋዲሳ መብራቴ

15 መድህኔ ታደሰ

ተጠባባቂዎች
30 ክብርአብ ዳዊት
6 አዲስአለም ተስፋዬ
22 መላኩ ወልዴ
9 አንተነህ ተሻገር
19 ዮሐንስ ሰገቦ
4 አስጨናቂ ሉቃስ
10 በረከት ይስሃቅ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *