ጋቶች ፓኖም አዲስ ክለብ አግኝቷል

ጋቶች ፓኖም አዲስ ክለብ አግኝቷል

ኢትዮጵያዊው አማካይ ኒውሮዝን ለቆ ሌላ ክለብ ተቀላቀሏል።

በተጠናቀቀው ውድድር ዓመት መጀመርያ ኢትዮጵያ መድንን ለቆ የኢራቁን ኒው ሮዝ የተቀላቀለው የተከላካይ አማካዩ ጋቶች ፓኖም በኢራቅ ፕሪምየር ሊግ ተሳታፊ ወደ ሆነው ወደ ሌላኛው ክለብ አል ናጃፍ መቀላቀሉ ክለቡ በይፋዊ ገፁ ገልጿል።

መድን ስሑል ሽረን ሦስት ለአንድ ካሸነፈበት የስምንተኛው ሳምንት ጨዋታ በኋላ መድንን ለቆ ወደ ኢራቁ ክለብ በማምራት ከክለቡ ጋር የወራት ቆይታ ያደረገው ግዙፉ አማካይ ከዚህ ቀደም በፋሲል ከነማ፣ የኢትዮጵያ ቡና፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ መቐለ 70 እንደርታ፣ ወላይታ ድቻ፣ ኤል ጎና፣ ሀራስ ኤል ሆዳድ እና አንዚ ማካቺካላ መጫወት የቻለ ሲሆን አሁን ደግሞ ለሌላኛውን የኢራቅ ክለብ በመፈረም የኤስያ ቆይታውን አራዝሟል።