የአጥቂ ስፍራ ተጫዋቹ አህመድ ሁሴን ከብሔራዊ ቡድኑ ጋር የማይገኝበትን ምክንያት ሶከር ኢትዮጵያ ማረጋገጥ ችላለች።
ከደቂቃዎች በፊት በድረገፃችን ሦስት ተጫዋቾች ወደ አሜሪካ የሚያመራውን የኢትዮጵና ብሔራዊ ቡድንን እንዳልተቀላቀሉ አስነብበናችሁ ነበር። ከእነኚህ ሦስት ተጫዋቾች መካከል አንዱ በመሆን ከብሔራዊ ቡድኑ ጋር የማይገኘው አህመድ ከብሔራዊ ቡድኑ ስብስብ ጋር አለመሆኑን በተመለከተ ሶከር ኢትዮጵያ ማጣራት አድርጋለች።
አህመድ ከብሔራዊ ቡድኑ ጋር የማይገኝበት ምክንያት ባደረግነው ማጣራት ከአንድ የግብፅ ክለብ ጋር ያደረገውን ድርድ ለመቋጨት እንደሆነ እና ዛሬ ወደ ካይሮ እንደሚያቀና አረጋግጠናል። አህመድ በግብፅ የሚኖረውን አጠቃላይ ሁኔታ አስመልክቶ ተከታታይ መረጃዎችን ወደ እናንተ የምናደርስ መሆኑን ከወዲሁ መጠቆም እንፈልጋለን። ተጫዋቹም ምናልባት በቀጣዮቹ ቀናት ብሔራዊ ቡድኑን እንደሚቀላቀል ይጠበቃል።
