የሴቶች ፕሪሚየር ሊግ | ሀዋሳ ከተማ እና አዲስ አዳጊው ሸገር ከተማ ተጫዋቾችን አስፈርመዋል

የሴቶች ፕሪሚየር ሊግ | ሀዋሳ ከተማ እና አዲስ አዳጊው ሸገር ከተማ ተጫዋቾችን አስፈርመዋል

በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የሚሳተፉት ሀዋሳ ከተማዎች አንድ ተጫዋች ሲያስፈርሙ ሸገር ከተማዎች በበኩላቸው ሦስት ተጫዋቾችን የግላቸው አድርገዋል።

ባሳለፍነው የውድድር አመት ካደረጓቸው 26 ጨዋታዎች ውስጥ 54 ነጥቦችን ሰብስበው ከአሸናፊው ጋር ጥሩ ፉክክርን በማድረግ ሁለተኛ ደረጃን ይዘው ያጠናቀቁት ሀዋሳ ከተማዎች ለቀጣዩ የውድድር ዘመን ይረዳቸው ዘንድ በሀዋሳ ከተማ ፣ ንግድ ባንክ ፣ መቻል ፣ አርባምንጭ ከተማ እንዲሁም ያለፈውን ዓመት በልደታ ክ/ከ ያሳለፈችው ግብጠባቂዋ ትዕግስት አበራ ሁለት አመት በሚቆይ ውል ለሀዋሳ ፊርማ አኑራለች።

የኢትዮጵያ ሴቶች ከፍተኛ ሊግ አሸናፊዎች ሸገር ከተማዎች በዝውውር መስኮቱ በንቃት እየተሳተፉ የሚገኙ ሲሆን በቅዱስ ጊዮርጊስ፣ አዲስ አበባ ከተማ እንዲሁም ያሳለፍነውን የውድድር ዓመት በመቻል ቤት ያሳለፈችውን ዓይናለም ዓለማየሁ በሁለት አመት ውል ሸገር ከተማን ተቀላቅላለች። ይህ በእንዲህ እንዳለ አማካኟን ወርቅነሽ ዘሪሁንን እና በአዳማና አርባምንጭ መጫወት የቻለችውን ግብ ጠባቂዋ ፎዚያ ዝናቡን በአንድ ዓመት ውል አስፈርመዋል።