👉”የሙከራ ዕድል ማግኘታቸውን ሰዎች በተለያየ መንገድ ሊተረጉሙት ይችላሉ።” አቶ ባሕሩ ጥላሁን
የአሜሪካ የኢግዚቪዥን ጉዟቸውን አጠናቀው በተመለሱት ዋልያዎቹ ቆይታ ዙሪያ ምን እየተባለ ነው?
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከዲሲ ዩናይትድ ጋር ያደረገውን ጨዋታ እና በዩናይትድ ስቴትስ የነበረውን አጠቃላይ ቆይታ አስመልክቶ ዛሬ በፌዴሬሽኑ መሰብሰብያ አዳራሽ ጋዜጣዊ መግለጫ እየተሰጠ ይገኛል። በቦታውም ከመገናኛ ብዙኀን የሄዳቹበትን ጉዞ ምን ያህል አሳክታችኋል እና ለሙከራ የተመረጡት አራት ተጫዋቾች ለምን በቀጥታ እንዲፈርሙ ማድረግ አልተቻለም? የሚሉትን ጥያቄዎች አስመልክቶ ዋና ስራ አስፈፃሚው አቶ ባሕሩ ጥላሁን ምላሽ ሰጥተዋል።
“ወደ አሜሪካ ስንሄድ ሦስት ነገሮችን ለማሳካት ነበር። አንደኛ በአሜሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን የማገናኘት የማስተሳሰር ጥሩ ድባብ የመፍጠር ዕቅድ ነበር በዚህ ረገድ አሳክተናል። ሁለተኛው ከብሔራዊ ቡድኑ ጋር አብረው የተጓዙ ተጫዋቾችን እዛው የመጫወት ዕድል እንዲያገኙ ማመቻቸት ነበር። በዚህ በኩልም አራት ተጫዋቾች የሙከራ ዕድል አግጋንተዋል። እንድያውም ስድስት የሚሆንበት ዕድል ነበር ግን ከዕድሜ ጋር ተያይዞ ዕድሜያቸው ከ29 ዓመት በላይ መሆኑን ተከትሎ ሳይሳካ ቀርቷል። ሌላው ከገቢ አንፃር ከፍተኛ ገንዘብ አግኝተናል። በጨዋታው በማሸነፋችን 75ሺ ዶላር ተገኝቷል ይህ ከዚህ ቀደም ብሔራዊ ቡድኑ ከሜዳው ውጪ ለሚያደርጋቸው የአፍሪካ፣ የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዎችን ወጪ እናወጣ ነበር አሁን ግን ትርፋ ሆነን መጥተናል። እንደ ፌዴሬሽን የሄድንበትን ዓላማ አሳክተን ተመልሰናል።” ካሉ በኋላ የሙከራ ዕድል ብቻ ከሚሆን በቀጥታ እንዲፈርሙ ማድረግ ለምን አልተቻለም ተብለው ሲጠይቁ የመለሱት አቶ ባሕሩ
“የሙከራ ዕድል ማግኘታቸውን ሰዎች በተለያየ መንገድ ሊተረጉሙት ይችላሉ ፤ ይህ የሰዎች አረዳድ ነው። በእኛ ዕይታ ከዚህ ቀደም እንደዚህ ያሉ መድረኮች የሉም ወደ አሜሪካ ወይም አውሮፓ ሄደው ሙከራ ማድረግ የሚችሉበት መድረኮች የሉም። በዚህ በኩል ይህ መድረክ ትልቅ ብሎ መውሰድ ይቻላል። ሙከራ ብቻ እንዳይሆን ተጫዋቾችን ትልቅ ስም ያላቸው አቅም ያለቸው እንደሆኑ ፌዴሬሽኑ ፕሮፋይላቸውን በደንብ እንዲያውቁ አድርጓል። በቀጣይ ከሙከራ ባለፈ በቀጥታ እንዲፈርሙ ለማድረግ እንሰራለን ብለዋል። />