👉 “ትልቅ ትምህርት ሰጥቶን ያለፈ ነው።” አቶ ባሕሩ ጥላሁን

👉 “ትልቅ ትምህርት ሰጥቶን ያለፈ ነው።” አቶ ባሕሩ ጥላሁን

👉”ቡድናችን ተሸንፎ ቢሆን ኖሮ ከባድ ታሪክ ይሆናል።”

👉 “ለወደፊቱ የተማርንባቸው ነገሮች ይኖራሉ።”

ከዲሲ ዩናይትድ አካዳሚ ቡድን ብሔራዊ ቡድኑ ክብር በማይመጥን መልኩ መጫወቱ ያለውን ሁኔታ አስመልክቶ አቶ ባሕሩ ምላሽ ሰጥተዋል።

የብሔራዊ ቡድኑ የአሜሪካ ቆይታን አስመልክቶ በአሁኑ ሰዓት የሚሰጠው መግለጫ የቀጠለ ሲሆን ከመገናኛ ብዙኀን በኩል የተለያዩ ጥያቄዎች እየተነሱ ይገኛል። በዋናነት ከአስተዳደር ጉዳይ ጋር በተያያዘ የሚነሱ ጥያቄዎች ጠንከር ብለው እየቀረቡ ሲሆን በተለይ ወደ አሜሪካ መጓዙ መልካም ቢሆንም ከዲሲ ዩናይትድ አካዳሚ ቡድን ብሔራዊ ቡድኑ ክብር በማይመጥን መልኩ መጫወቱ ያለውን ሁኔታ አስመልክቶ አቶ ባሕሩ ምላሽ ሰጥተዋል።

“አስቀድመን ከአካዳሚ ቡድኑ ጋር እንደምንጫወት መረጃ አልነበረንም። የጨዋታው ጅማሬ ላይ የደረሰን የተጫዋቾች ስም ዝርዝር ላይ እና የወጣው አሰላለፍ የተለያየ ነው። በኋላ እኛም በማህበራዊ ሚዲያ ነው የተመለከትነው እዚህ ላይ ውሳኔው የአሰልጣኙ ነው ሊጠቀምባቸው የሚችሉትን ተጫዋች መምረጥ ምርጫ የእርሱ ነው። ከሁለተኛ ቡድን ተጫዋቾች ቢገቡም ወደ ስድስት የሚጠጉ የዋናው ተጫዋቾች ተሰልፈው ነበር። ይሄም ሆኖ ቡድናችን ተሸንፎ ቢሆን ኖሮ ከባድ ታሪክ ይሆናል። ለወደፊቱ ግን ምን የተማርንባቸው ነገሮች ይኖራሉ። ትልቅ ትምህርት ሰጥቶን ያለፈ ነው።” ብለዋል