የሴቶች ፕሪሚየር ሊግ | ድሬዳዋ ከተማዎች ተጫዋቾችን ማስፈረም ጀምረዋል

የሴቶች ፕሪሚየር ሊግ | ድሬዳዋ ከተማዎች ተጫዋቾችን ማስፈረም ጀምረዋል

በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የሚሳተፈው ድሬዳዋ ከተማ ሦስት አዳዲስ ተጫዋቾችን ሲያስፈርም የሶስት ነባር ተጫዋቾችን ውል አድሷል።

ያሳለፍነውን የውድድር  አመት በሀምበሪቾ ያሳለፉት የተከላካይ ስፍራ ተጫዋቾች ዝናሽ ሰለሞን እና ፍሬነሽ ዮሐንስ እንዲሁም በውድድር አመቱ ለልደታ ክ/ከ ተጫውታ ያሳለፈችው የመሀል ተከላካዩዋ ስሜነሽ ንጉሤ ክለቡን  የተቀላቀሉ ተጫዋቾች ናቸው።

አዲስ ካስፈረማቸው ተጫዋቾች ባለፈ የቡድኑን ነባር ተጫዋቾች ውል ማደስ የጀመረው ክለቡ ግብ ጠባቂዋን ሂሩት ደሴ፣ የአማካይ ስፍራ ተጫዋቿ ይዲዲያ አጫ እና የቀኝ መስመር ተከላካይ ተጫዋቿ ዓይናለም አደራ ለተጨማሪ ዓመት የሚያቆያቸውን ውል አድሰዋል።