ቡናማዎቹ ስብሰባቸውን ማጠናከር ቀጥለዋል

ቡናማዎቹ ስብሰባቸውን ማጠናከር ቀጥለዋል

በዝውውሩ የነቃ ተሳትፎ እያደረገ የሚገኘው ኢትዮጵያ ቡና አጥቂውን ሦስተኛ ፈራሚ አድርጎታል።

ባለፈው የውድድር ዓመት ሳይጠበቁ የዋንጫ ተፎካካሪ ሆነው በስተመጨረሻም ሁለተኛ ደረጃን ይዘው ለማጠናቀቅ የተገደዱት ኢትዮጵያ ቡናዎች ፌዴሬሽኑ ባወጣው የአሰልጣኝነት ፍቃድ ደረጃ ምክንያት ከዋና አሰልጣኛቸው ነጻነት ክብሬ ጋር ተለያይተው ምክትል አሰልጣኛቸው የነበረውን ዐቢይ ካሣሁን በዋና አሰልጣኝነት መሾማቸው ይታወቃል። አሰልጣኙም ቀደም ብለው ወደ ዝውውር በመግባት ከዘላለም አባተ እና ከናይጄሪያዊው አዳሙ አቡበከር በመቀጠል ሦስተኛ ተጫዋቻቸውን አስፈርመዋል።

ቡድኑን የተቀላቀለው በረከት ብርሃኑ ነው። በአዲስ ከተማ የእግርኳስ ጅማሬውን አድርጎ በኢትዮ ኤሌክትሪክ ፤ ያለፈውን ዓመት ደግሞ በሶሎዳ አድዋ ያሳለፈው አጥቂው በኢትዮጵያ ቡና ለቀጣዮቹ ሁለት ዓመታት የሚቆይበትን ውል ፈርሟል።