የመሳይ አገኘሁን ውል ያራዘሙት ባህር ዳሮች የመጀመርያ ፈራሚ ተጫዋችን አግኝተዋል።
በአሰልጣኝ ደግአረገ ይግዛው እየተመሩ ለከርሞ ውድደር የሚቀርቡት ባህር ዳር ከተማዎች ከደቂቃዎች በፊት የመስመር ተከላካያቸውን መሳይ አገኘውን ውል ለሁለት ዓመታት ማራዘማቸውን ይፋ አድርገው ነበር። አሁን ደግሞ የፊት አጥቂ በማስፈረም ወደ ዝውውሩ ገብተዋል።
ለጣና ሞገዶቹ ፊርማውን ያኖረው ዮሐንስ ደረጄ ነው። በመቻል ከታዳጊ ቡድን እስከ ዋናው ቡድን መጫወት የቻለው አጥቂው በከፍተኛ ሊግ የተለያዩ ክለቦች ተጫውቶ ያሳለፈ ሲሆን በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን በእንጅባራ ከተማ ባሳየው ድንቅ እንቅስቃሴ በአጋማሹ የዝውውር መስኮት ድሬዳዋ ከተማን በመቀላቀል በፕሪሚየር ሊጉ ራሱን በጥሩ ሁኔታ ያስተዋወቀ አጥቂ ነበር።
