ሸገር ከተማ የዝውውር መስኮቱ ስምንተኛ ፈራሚውን አግኝቷል
በዝውውር መስኮት የነቃ ተሳትፎ በማድረግ ላይ የሚገኘው አዲስ አዳጊው ሸገር ከተማ የዝውውር መስኮቱ ስምንተኛው ፈራሚው አግኝቷል። ከዚህ ቀደም ካሌብ በየነ፣ ቡልቻ ሹራ፣ ዓብዱልበሲጥ ከማል፣ ገመደ ማሞ፣ ከቤ ብዙነህ፣በረከት ወልዴ እና ባህሩ ነጋሽን ያስፈረመው ቡድኑ አሁን ደግሞ አጥቂው ፀጋዬ ብርሃኑን አስፈርሟል።
ከዚህ ቀደም በወላይታ ድቻ ታዳጊ እና ዋናው ቡድንእንዲሁም ሀድያ ሆሳዕና የተጫወተው የፊት መስመር ተሰላፊው በድጋሜ ወደ እናት ክለቡ ወላይታ ድቻ ተመልሶ ቆይታ ካደረገ በኋላ አሁን ወደ አዲስ አዳጊው ቡድን ለመቀላቀል ፌርማውን አኑሯል።