ናትናኤል ገብረጊዮርጊስ ወደ አሳዳጊ ክለቡ ሊመለስ ነው።
ቀደም ብለው አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌን ሾመው ግብ ጠባቂውን ሞየስ ፖዎቲን ለማስፈረም የተስማሙት ፋሲል ከነማዎች አሁን ደግሞ የቀድሞ ተጫዋቻቸው ናትናኤል ገብረጊዮርጊስን ለማስፈረም ከጫፍ ደርሰዋል።
ከዐፄዎቹ ታዳጊ ቡድን ተገኝቶ ዋናውን ቡድንን አራት ዓመታት ካገለገለ በኋላ ባለፈው የውድድር ዓመት ወደ ኢትዮ ኤሌክትሪክ አምርቶ ቡድኑን በአጥቂነት እና በአማካይነት ያገለገለው ተጫዋቹ ከአንድ ዓመት የኤልፓ ቆይታ በኋላ ወደ እናት ክለቡ ለመመለስ ከስምምነት ደርሷል።