አርባምንጭ ከተማዎች ወደ ዝውውሩ በመግባት የቀድሞ አማካይ ተጫዋቻቸውን ዳግም ለማስፈረም ተስማምተዋል።
በአሰልጣኝ በረከት ደሙ የሚመሩት አርባምንጭ ከተማዎች የስምንት የነባር ተጫዋቾቻቸውን ውል በማራዘም ስራዎችን እየሰሩ ሲሆን በመቀጠልም ስብስባችን ለማጠናከር ወደ ዝውውሩ በመግባት የቀድሞ አማካይ ተጫዋቻቸውን አማኑኤል ጎበናን ለማስፈረም ተስማምተዋል።
ባለብዙ ልምዱ አማካይ በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት ከሀዋሳ ከተማ ጋር ያሳለፈ ሲሆን ከዚህ ቀደም በሀድያ ሆሳዕና ፣ አዳማ ከተማ ተጫውቷል። አሁን አማካዩ ከሰባት ዓመት በኋላ ወደ ቀድሞ ክለቡ አርባምንጭ ከተማ መመለስ የሚያስችለውን ስምምነት መፈፀሙን አውቀናል።
አሰልጣኝ በረከት በቀጣይ ቀናት ቡድናቸውን ለማጠናከር በዝውውሩ በስፋት እንደሚገቡ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።