ቢጫዎቹ ተጨማሪ ተጫዋች አስፈርመዋል

ቢጫዎቹ ተጨማሪ ተጫዋች አስፈርመዋል

ቀደም ብለው ፍሬው ሰለሞንን ያስፈረሙት ወልዋሎዎች አሁን ደግሞ ተጨማሪ ተጫዋች የግላቸው አድርገዋል።

ቀደም ብለው አማካዩ ፍሬው ሰለሞንን የክረምቱ የመጀመርያ ፈራሚያቸው ያደረጉት ቢጫዎቹ አሁን ደግሞ አማካይ አስፈርመዋል።

ወደ ቡድኑ የተቀላቀለው ተጫዋች ደግሞ አማካዩ በየነ ባንጃው ነው። ከአፍሮ ፅዮን ከ17 ዓመት በታች ቡድን የተገኘው እና ከዛ ቀጥሎ ኢትዮጵያ ቡና ታዳጊ ቡድን፣ በኢትዮጵያ ከ17 ዓመት እንዲሁም ከ 20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን፣ በገላን ከተማ እንዲሁም ያለፉትን ሁለት ዓመታት በሀድያ ሆሳዕና ቆይታ ያደረገው ተጫዋቹ ባለፈው የውድድር ዓመት በ27 ጨዋታዎች ተሳትፎ 1373 ደቂቃዎች ነብሮቹን ያገለገለ ሲሆን አሁን ደግሞ ከቀድሞ አሰልጣኙ ጋር አብሮ ለመስራት ወደ ወልዋሎ አምርቷል።