ቢጫዎቹ በዝውውሩ መሳተፋቸውን ቀጥለዋል

ቢጫዎቹ በዝውውሩ መሳተፋቸውን ቀጥለዋል

ወልዋሎዎች አንድ ተጫዋች አስፈርመው የአንድ ነባር ተጫዋች ውል አራዝመዋል።

ቀደም ብለው አሰልጣኝ ግርማ ታደሰን በዋና አሰልጣኝነት ቀጥረው በዛሬው ዕለት አማካዮቹ ፍሬው ሰለሞን እና በየነ ባንጃውን ያስፈረሙት ወልዋሎዎች አሁን ደግሞ የኪሩቤል ወንድሙን ውል አራዝመው ኢብራሂም መሐመድን አስፈርመዋል።

ባለፈው የውድድር ዓመት ቡድኑን ተቀላቅሎ በ30 ጨዋታዎች ተሳትፎ 2553′ ደቂቃዎችን ያገለገለው የቀድሞ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ለገጣፎ ለገዳዲ የግራ መስመር ተከላካዩ ኪሩቤል ወንድሙ ከቡድኑ ጋር ለተጨማሪ ዓመት ለመቆየት ውል ያራዘመ ተጫዋች ሲሆን በመቻል ታዳጊ እና ዋናው ቡድን የተጫወተው ወጣቱ የፊት መስመር ተጫዋች ኢብራሂም መሐመድ ደግሞ የወልዋሎ የክረምቱ ሦስተኛ ፈራሚ በመሆን ቡድኑን ተቀላቅሏል።