ነብሮቹ የተከላካያቸውን ውል ለማራዘም ተስማሙ

ነብሮቹ የተከላካያቸውን ውል ለማራዘም ተስማሙ

አይቮርያኑ ከነብሮቹ ጋር ለመቆየት ከስምምነት ደርሷል።

ቀደም ብለው አሰልጣኝ ካሊድ መሐመድን በዋና አሰልጣኝነት በመቅጠር አሸናፊ ኤልያስ፣ ሙሴ ካቤላ እና ኤልያስ አሕመድን ለማስፈረም የተስማሙት ነብሮቹ አሁን ደግሞ የአይቮርያኑ ተከላካይ ካሉዱ ኩሊባሊን ውል ለማራዘም ተስማምተዋል።

ያለፉትን ሁለት የውድድር ዓመታት በነብሮቹ ቤት ቆይታ የነበረው እና ዘለግ ላሉ ዓመታት በኢትዮጵያ እግር ኳስ ላይ የቆየው አይቮርያኑ ተከላካይ ከዚህ ቀደም በደደቢት እና ፋሲል ከነማ መጫወቱ የሚታወስ ሲሆን አሁን ደግሞ ለሦስተኛ ዓመት በሀድያ ሆሳዕና መለያ ለመጫወት ውሉን ለማራዘም ከስምምነት ደርሷል።