ኢትዮጵያ ቡና ጠንካራውን ተከላካይ ለማስፈረም ተስማማ።
አስቀደመን ባደረስናችሁ መረጃ መሰረት ሁለት ክለቦች ሀዋሳ ከተማ እና ኢትዮጵያ ቡና ራምኬል ጀምስን ለማስፈረም መፋጠጣቸውን አሳውቀን ነበር። አሁን ባገኘነው መረጃ ከሆነ ኢትዮጵያ ቡና ድርድሩን አሸንፎ ራምኬልን ለማስፈረም መስማማቱን አውቀናል።
በትውልድ ሀገሩ ጋምቤላ ከተማ እግር ኳስን በክለብ ደረጃ በመጫወት የጀመረው እና ከአምሰት ዓመት በፊት ጉለሌ ክፍለ ከተማን በከፍተኛ ሊጉ አምበል ሆኖ በመሀል ተከላካይነት ያገለገለው ተጫዋቹ በሦስት ዓመታት ውል ቡናማዎቹን በመቀላቀል ያሳለፈ ሲሆን በተለይ ዘንድሮ ለቡድኑ በ30 ጨዋታዎች 2655 ደቂቃዎች ያገለገለ ሲሆን የ2017 የውድድር ዘመን ለኮከብነት ከታጩ አምስት ተጫዋቾች መካከል አንዱም ነበር። ራምኬል በኢትዮጵያ ቡና ለተጨማሪ ሁለት ዓመታት የሚቆይ ይሆናል።