የወቅቱ ሊጉ ኮከብ ተጫዋች ማረፊያው የት ይሆን?

የወቅቱ ሊጉ ኮከብ ተጫዋች ማረፊያው የት ይሆን?

በአራት ዓመታት ውስጥ ሦስት ጊዜ የሊጉን ዋንጫ ከፍ አድርጎ ማንሳት የቻለውን ተጫዋች ለማስፈረም ሁለት ክለቦች ተያይዘዋል።

ከሦስት ክለቦች ጋር አራት የሊጉን ዋንጫ ማሳካት የቻለው የ2017 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኮከብ ተጫዋች ሀይደር ሸረፋ ከኢትዮጵያ መድን ጋር ያለው የውል ዘመን መጠናቀቁን ተከትሎ በቻምፒዮኖቹ ቤት ለመቆየት የነበረው ፍላጎት ሳይሳካ ቀርቷል።

ይህን ተከትሎ ኮከቡን ተጫዋች ለማስፈረም የቀድሞ ክለቦቹ መቐለ 70 እንደርታ እና አዳማ ከተማ የግላቸው ለማድረግ መቃረባቸውን ለማወቅ ችለናል። በግል ጉዳይ ከተጫዋቹ ጋር የተስማሙት ክለቦቹ ምን አልባትም ዝውውሩ ሀይደር ከብሔራዊ ቡድኑ ልምምድ በኋላ ዛሬ ወይም ነገ ከሁለት አንዱ ቡድን ጋር የሚጨርስ ይሆናል።