ባለፉት ዓመታት በሀምራዊ ለባሾቹ ቤት ቆይታ የነበረው አማካይ ወደ መቐለ 70 እንደርታ ለማምራት ተቃርቧል።
በአሰልጣኝ ጌታቸው ዳዊት መሪነት ለ2018 የውድድር ዓመት ቡድናቸውን ለማጠናቀር በእንቅስቃሴ ላይ ያሉትና ቀደም ብለው አራት ተጫዋቾችን ለማስፈረም የተስማሙት መቐለ 70 እንደርታዎች አሁን ደግሞ ባለፉት ዓመታት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጥሩ ቆይታ የነበረውን ተከላካይ አማካዩ ብሩክ እንዳለን ለማስፈረም ከስምምነት ደርሰዋል።
ከዚህ ቀደም በለገጣፎ ለገዳዲ፣ ገላን ከተማ፣ እንዲሁም ከ2015 ጀምሮ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቆይታ የነበረውና ሀምራዊ ለባሾቹ ወደ ፕሪምየር ሊጉ ስያድጉም ሆነ የሊጉ ሻምፕዮን ሲሆኑ ጉልህ ድርሻ ከነበራቸው ተጫዋቾች የሚጠቀሰው ተጫዋቹ በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በ28 ጨዋታዎች ተሳትፎ 2346′ ደቂቃዎች ቡድኑን ማገልገሉ የሚታወስ ሲሆን አሁን ደግሞ ለቀናት ካደረገው ድርድር በኋላ አመሻሹን የሕክምና ምርመራው አጠናቆ ወደ መቐለ ለማምራት ከጫፍ ደርሷል።