ምዓም አናብስት የመሀል ተከላካዩን የግላቸው ለማድረግ ተቃርበዋል

ምዓም አናብስት የመሀል ተከላካዩን የግላቸው ለማድረግ ተቃርበዋል

ቁመታሙ ተከላካይ ከስድስት ዓመታት የሲዳማ ቡና ቆይታ በኃላ መቐለ 70 እንደርታን ለመቀላቀል ከጫፍ ደርሷል

ባለፉት ቀናት አምስት ተጫዋቾች የግላቸው ለማድረግ የተስማሙት መቐለ 70 እንደርታዎች አሁን ደግሞ ባለፉት ስድስት ዓመታት በሲዳማ ቡና ቆይታ የነበረው የመሀል ተከላካዩ ጊት ጋት ኩትን ለማስፈረም ተቃርበዋል። በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በ21 ጨዋታዎች ተሳትፎ 1692′ ደቀቃዎችን ቡድኑን ያገለገለው ተጫዋቹ በ2011 አዲስ አበባ ከተማን ለቆ ወደ ክለቡ ካቀና በኋላ ያለፉትን ስድስት ዓመታት በሲዳማ ቡና መለያ ሲጫወት ከቆየ በኋላ ከክለቡ ጋር ያለውን ውል መጠናቀቁን ተከትሎ ወደ መቐለ 70 እንደርታ ለማምራት ከስምምነት ደርሷል።

በግንቦት 22 2014 በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን መለያ የመጀመርያ ጨዋታውን ያደረገው ቁመታሙ ተከላካይ በቻን ጨምሮ በዓለም ዋንጫ እና አፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ጨዋታዎች ላይ ሀገሩን አገልግሏል።