ቢጫዎቹ የወጣት ተጫዋቾቹን ውል ለማራዘም ተስማምተዋል።
አሰልጣኝ ግርማ ታደሰን ቀጥረው ፍሬው ሰለሞን፣ በየነ ባንጃው፣ ኢብራሂም መሐመድ ፣ ፍሬዘር ካሳ፣ ሰመረ ሃፍታይ፣ ጌትነት ተስፋየ፣ ፍቃዱ መኮንን፣ ነፃነት ገብረመድህን እና ሙሉዓለም መስፍን ለማስፈረም ተስማምተው የኪሩቤል ወንድሙን ውል ያራዘሙት ወልዋሎዎች አሁን ደግሞ ከሁለተኛ ቡድን አድገው በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት ቡድኑን ያገለገሉ ሦስት ተጫዋቾችን ውል ለማራዘም ተስማምተዋል።
ከቡድኑ ጋር ለመቀጠል የተስማሙት ደግሞ በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በዘጠኝ ጨዋታዎች ተሳትፎ 780′ ደቂቃዎች ቡድኑን ያገለገለው ተስፈኛው ግብ ጠባቂው ናትናኤል ኪዳኔ፤ በ22 ጨዋታዎች ተሳትፎ 1674′ ደቂቃዎችን ቡድኑን በወጥነት ያገለገለው ወጣቱ የቀኝ መስመር ተከላካይ ናሆም ኃይለማርያም እንዲሁም በ27 ጨዋታዎች ተሳትፎ 1821′ ደቂቃዎች ቡድኑን ያገለገለው የፊት መስመር ተጫዋቹ ዳዊት ገብሩ ናቸው።