ምዓም አናብስት የፊት መስመር ተጫዋቹን ለማስፈረም ከስምምነት ደርሰዋል

ምዓም አናብስት የፊት መስመር ተጫዋቹን ለማስፈረም ከስምምነት ደርሰዋል

በስሑል ሽረ ቆይታ የነበረው ተጫዋች ወደ ምዓም አናብስት ለመቀላቀል ከጫፍ ደርሷል።

በ2018 የውድድር ዓመት ቡድናቸውን ለማጠናከር በእንቅስቃሴ ላይ ያሉትና ቀደም ብለው አምስት ተጫዋቾችን ለማስፈረም የተስማሙት መቐለ 70 እንደርታዎች አሁን ደግሞ በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በስሑል ሽረ መለያ ጥሩ እንቅስቃሴ ያደረገው የፊት መስመር ተሰላፊውን ብርሃኑ አዳሙ ለማስፈረም ከስምምነት ደርሰዋል።

በስሑል ሽረ ቆይታው በ31 ጨዋታዎች ተሳትፎ 8 ግቦች ማስቆጠር የቻለው ተጫዋቹ ለቀናት ካደረገው ዘለግ ያለ ድርድር በኋላ ዛሬ ከስምምነት ደርሶ የሕክምና ምርመራውን ማጠናቀቁን ተከትሎ ከቀድሞ አሰልጣኙ ጋር በድጋሚ ለመስራት ወደ ምዓም አናብስቱ ቤት ለማምራት ተስማምቷል።
ተጫዋቹ በ2009 ከአርባምንጭ ታዳጊ ቡድን ወደ ዋናው ቡድን ካደገ በኋላ ባለፉት ዓመታት ለአርባምንጭ ዋናው ቡድን፣ ሀምበሪቾ፣ ወሎ ኮምቦልቻ፣ ባቱ ከተማ እንዲሁም በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በስሑል ሽረ መጫወቱ ይታወሳል።