ወጣቱ ተከላካይ ሽረ ምድረ ገነትን ተቀላቀለ

ወጣቱ ተከላካይ ሽረ ምድረ ገነትን ተቀላቀለ

በአሰልጣኝ ዳንኤል ፀሐዬ የሚመራው ሽረ ምድረ ገነት ቡድኑን ማጠናከሩን ቀጥሎበታል።

በትናንትናው ዕለት ወደ ዝውውሩ ገብተው መክብብ ደገፉ፣ ተካልኝ ደጀኔ እና በኃይሉ ግርማን ያስፈረሙት ሽረ ምድረ ገነቶች አሁን ደግሞ በዝውውር መስኮቱ አራተኛ ፈራሚያቸውን አግኝተዋል። ቡድኑን የተቀላቀለው ደግሞ ወጣቱ ተከላካይ ፀጋአብ ዮሐንስ ነው።

ከሀዋሳ ከተማ ታዳጊ ወደ ዋናው ቡድን አድጎ ባለፉት ስድስት ዓመታት አሳዳጊ ክለቡን ያገለገለው የመሃል ተከላካዩ ከሐይቆቹ ጋር ያለው ውል መጠናቀቁን ተከትሎ ማረፍያው በአሰልጣኝ ዳንኤል ፀሐዬ የሚሰለጥነው ሽረ ምድረ ገነት ሆኗል።