ኢትዮጵያዊው አማካይ ከሊቢያው ክለብ ጥያቄ ቀርቦለታል።
በተጠናቀው ዓመት መጀመርያ መቻልን በመልቀቅ ወደ ሊብያው አል መዲና ካቀና በኋላ በክለቡ መለያ ባደረጋቸው ስምንት ጨዋታዎች ሦስት ግቦች ካስቆጠረ በኋላ የትሪፖሊውን ክለብ በመልቀቅ ወደ ሌላኛው የሊብያ ፕሪምየር ሊግ ተሳታፊ ሸባብ አል ጋሀር በመቀላቀል በሀገሪቱ ቆይታው በ14 ጨዋታዎች ስድስት ግቦች ያስቆጠረው አማካዩ ከነአን ማርክነህ ከሸባል አል ግሀር የውል ማራዘምያ ጥያቄ ቀርቦለታል።
ኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአሜሪካ ቆይታው ከዲሲ ዩናይትድ ጋር ባደረገው ጨዋታ በመልማዮች ዓይን ውስጥ የገባው ተጫዋቹ ከሊብያው ክለብ የውል ማራዘም ጥያቄ እንደቀረበለት ሆኖም እስካሁን ድረስ ውሳኔ ላይ እንዳልደረሰም ለሶከር ኢትዮጵያ ገልጿል።
በተጨማሪም የሀገር ውስጥ ክለቦች ከነዓን ለማስፈረም ንግግር የጀመሩ እንዳለ ሰምተናል።