ቢንያም በላይ ከቀጣዩ ጨዋታ ውጭ ሆኗል

ቢንያም በላይ ከቀጣዩ ጨዋታ ውጭ ሆኗል

ዋልያዎቹ ከሴራሊዮን ጋር ለሚደርጉት ጨዋታ የወሳኙን ተጫዋች ግልጋሎት አያገኙም።


በአፍሪካ ሀገራት የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ከግብፅ፣ ቡርኪና ፋሶ፣ ሴራሊዮን፣ ጊኒ ቢሳው እና ጅቡቲ ጋር በአንድ ምድብ የተደለደለው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ካደረጋቸው 7 ጨዋታዎች ውስጥ አንዱን በማሸነፍ በሶስቱ አቻ በመውጣት በሶስቱ ተሸንፈው በአጠቃላይ 6 ነጥቦችን በመሰብሰብ 5ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።

ባሳለፍነው አርብ በአፍሪካ ሀገራት የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ከግብጽ ብሔራዊ ቡድን ጋር ጨዋታቸውን ያደረጉት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በሙሀመድ ሳላ እና ኦማር ማርሙሽ የፍፁም ቅጣት ምት ግቦች 2-0 መሸነፋቸው የሚታወስ ሲሆን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋች የሆነው ቢንያም በላይ ከጊኒ ቢሳው እና ከግብፅ ጋር በነበረው ጨዋታ ሁለት ቢጫ ካርዶችን መመልከቱን ተከትሎ ማክሰኞ ከ ሴራሊዮን ጋር የሚደረገው ጨዋታ በቅጣት ምክንያት የሚያልፈው ይሆናል።