ለብዙ ዓመታት ተስፈኛ እግርኳሰኞችን በማሳደግ የሚታወቀው ሀዋሳ ከተማ ከተስፋ ቡድን እና ከሰመር ካፕ ውድደር ተጫዋቾችን ወደ ቡድኑ ቀላቅሏል።
በአሰልጣኝ ተመስገን ዳና እየተመሩ ከቀናት በፊት ዝግጅታቸውን በመቀመጫ ከተማቸው የጀመሩት ሀዋሳ ከተማዎች አዳዲስ እና ነባር ተጫዋቾች እንዳስፈረሙ ሁሉ አሁን ደግሞ ከተስፋ ቡድን ወደ ዋናው ቡድን አስር ተጫዋቾች እና ሀዋሳ ላይ ከተካሄደው የሰመር ካፕ ውድደር ላይ ደግሞ ሁለት ተጫዋቾችን መውሰዱን ከክለቡ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ክለቡን የተቀላቀሉት ተስፋኛ ወጣቶች ተከላካይ መንግስተአብ ማርቆስ፣ እስራኤል ሰማያት፣ ሕገአብ ካሳሁን እና የአብሥራ ደግፌ እንዲሁም ዚያድ ከድር፣ ዳግም ትንሣኤ ፣ ይደግልኝ አሰፋ፣ ምንተስኖት ቶማስ እና ሀብታሙ ገናን አጥቂዎችን ሲያሳድግ ከሰመር ካፕ የግራ መስመር ተከላካይ ዳንኤል ዘርፉ እና አጥቂ ዮርዳኖስ ፀጋዬ ቡድኑን መቀላቀላቸውን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።