ወጣቱ አማካይ ወደ ፋሲል ከነማ አምርቷል።
በአዳማ ከተማ ዝግጅታቸውን የጀመሩት ፋሲል ከነማዎች ቡድናቸውን ለማጠናከር የምኞት ደበበን ውል ካራዘሙ በኋላ የግብ ጠባቂ ሞይስ ፓዎቲ፣ የአብዱላዚዝ አማን፣ የናትናኤል ገብረጊዮርጊስ እና ያሬድ ብርሃኑን ዝውውር ማጠናቀቃቸው ይታወሳል። አሁን ደግሞ አማካዩን አቤኔዘር ዮሐንስን ማስፈረማቸው ታውቋል።
የእግርኳስ ሕይወቱን በሀዋሳ ከተማ የጀመረው አማካዩ ያለፉትን ዓመታት ከታዳጊ ቡድን እስከ ዋናው ቡድን ድረስ ለሀዋሳ ከተማ አገልግሎት ሰጥቷል። በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በ28 ጨዋታዎች ተሳትፎ 1559 ደቂቃዎች ቡድን ያገለገለ ሲሆን በሚያገኛቸው የመጫወት አጋጣሚዎች በስሙ አራት ጎሎችን ማስቆጠር ችሏል። አቤኔዘር ለረጅም ዓመት ካገለገለበት አሳዳጊ ቤቱ ወጥቶ አሁን መዳረሻው ዐፄዎቹ ቤት ሆኗል።