ነብሮቹ አማካይ አስፈረሙ

ነብሮቹ አማካይ አስፈረሙ

ባለፉት አምስት ዓመታት በብርቱካናማዎቹ ቤት ቆይታ የነበረው ተጫዋች ከአምስት ዓመታት በኋላ ወደ ቀድሞ ክለቡ አምርቷል።

በዝውውር መስኮቱ አሸናፊ ኤልያስ፣ ሙሴ ከቤላ እና ኤልያስ አሕመድን ጨምሮ በዝውውር መስኮቱ ስምንት ተጫዋቾችን በማስፈረም የነባሮቹን ውል ያራዘሙት በአሰልጣኝ ካሊድ መሐመድ የሚመሩር ሀዲያ ሆሳዕናዎች አሁን ደግሞ ከዚህ ቀደም በክለቡ ቆይታ የነበረው አማካዩ ሱራፌል ጌታቸውን አስፈርመዋል።

በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በ23 ጨዋታዎች ተሳትፎ 1246′ ደቂቃዎች ቡድኑን ያገለገለው ተጫዋቹ ከዚህ ቀደም በአዳማ ከተማ፣ አዲስ አበባ ከተማ እና ሀዲያ ሆሳዕና መጫወቱ የሚታወስ ሲሆን አሁን ደግሞ ያለፉትን አምስት ዓመታት የቆየበትን ድሬዳዋ ከተማን በመልቀቅ ከአምስት ዓመታት በኋላ ወደ ሀዲያ ሆሳዕና ተመልሷል።