ሀዲያ ሆሳዕናዎች ጋናዊውን ግብ ጠባቂ ለማስፈረም ከስምምነት ደርሰዋል።
ከቀናት በፊት አማካዩ ሱራፌል ጌታቸውን ወደ ቡድናቸው የቀላቀሉት በአሰልጣኝ ካሊድ መሐመድ የሚመሩት ሀዲያ ሆሳዕናዎች ጋናዊ ግብ ጠባቂ ለማስፈረም ከስምምነት ደርሰዋል።
ወደ ቡድኑ ለማምራት ከስምምነት የደረሰው ተጫዋች ደግሞ ግብ ጠባቂው አንድሪውስ ኦውሱ ነው። በሀገሩ ክለብ አክራ ላዮንስ የአራት ዓመት ቆይታ ካደረገ በኋለ ባለፈው የውድድር ዓመት ወደ ሞልዶቫ አቅንቶ በሀገሪቱ ‘ሱፐር ሊጋ’ ተሳታፊ በነበረው ሲ ኤስ ኤፍ ስፓርታኒ ስፖርቱል ሰሌመት ቆይታ የነበረው ወጣቱ ግብ ጠባቂ አሁን ደግሞ ወደ ሀዲያ ሆሳዕና ለማምራት ከስምምነት ደርሷል።
የግብ ዘቡ ዛሬ አዲስ አበባ የገባ ሲሆን በቀናት ውስጥ የዝውውር ሂደቱን የሚያጠናቅቅ መሆኑን ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል።