ያለፉትን ዓመታት በፈረሰኞቹ ቤት ቆይታ የነበው አጥቂ አዲስ ክለብ ለመቀላቀል ተቃርቧል።
በምድብ አንድ ተደልድለው አዳዲስ ተጫዋቾችን በማስፈረም እና የነባር ተጫዋቾችን ውል በማራዘም ቅድመ ውድድር ዝግጅታቸው በአዳማ ከተማ እያደረጉ የሰነበቱት አዲስ አዳጊዎቹ ሸገር ከተማዎች ወጣቱን አጥቂ ዳግማዊ አርአያን ለማስፈረም መቃረባቸውን አውቀናል።
ያለፉትን ዘጠኝ ዓመታት በቅዱስ ጊዮርጊስ ከታዳጊ ቡድን እስከ ዋናው ቡድን ተጫውቶ ያሳለፈው ዳግማዊ ሁለት የፕሪሚየር ሊጉ እንዲሁም አንድ የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ካነሳበት ክለቡ ጋር ዘንድሮ ውሉን ማጠናቀቁን ተከትሎ ለሸገር ከተማ ለአንድ ዓመት ለመቆየት ተስማምቷል።