ሲዳማ ቡና ካሜሮናዊ አጥቂ አስፈርሟል

ሲዳማ ቡና ካሜሮናዊ አጥቂ አስፈርሟል

ዩጋንዳዊ የግብ ዘብ ያስፈረመው ሲዳማ ቡና ካሜሮናዊውን አጥቂ ማስፈረማቸው ታውቋል።

በአንደኛው ምድብ ተደልድለው የ2018 የውድድር ዘመን የመክፈቻ ጨዋታቸውን በመቀመጫ ከተማቸው የፊታችን ቅዳሜ ከወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርስቲ ጋር የሚያከናውኑት ሲዳማ ቡናዎች አሁን ደግሞ ሁለተኛ የውጭ ሀገር ዜግነት ያለው ተጫዋች አስፈርመዋል።

ካሜሮናዊ አጥቂ ቡድኑን የተቀላቀለው ተጫዋች ብሌዝ ንጎህ ሲሆን ከዚህ ቀደም ለሀገሩ ክለቦች ዩኒየን ዶውላ እና ዳይናሞ ዶውላ መጫወቱ ሲታወቅ አሁን መዳረሻውን ሲዳማ ቡና አድርጓል።