የፊፋ የፕሮፌሽናል ተጫዋቾች ማኅበር የምክክር መድረክ ላይ እንዲገኙ ለሁለቱ ኢትዮጵያውያን ጥሪ ቀርቦላቸዋል።

ዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ማኅበር (ፊፋ) የፕሮፌሽናል ተጫዋቾችን ደህንነት፣ ደመወዝ፣ የውል ጉዳዮች እና ሌሎች በዘመናዊ እግር ኳስ የሚያጋጥሙ ችግሮች ዙሪያ ምክክር ለማድረግ በሞሮኮ ራባት የሚካሄድ ፕሮግራም አዘጋጅቷል። ሆኖም በርካታ የተጫዋቾች ተወካዮች በመድረኩ በመሳተፍ የወከሏቸው ተጫዋቾች ከላይ የጠቀስናቸውን ጨምሮ በዘመናዊ እግርኳስ የሚያቀርቧቸውን ጥያቄዎች አቅርበው ምላሽ እንደሚሰጣቸው የሚጠበቅ ሲሆን ይህ ጥሪም ለሀገራችን እግርኳስ ተጫዋቾች ትልቅ የጥያቄ ነጻነት እና የመብት ማስከበር ለውጥ እንደሚያመጣ ይጠበቃል።
ፊፋ ለመጀመሪያ ጊዜ የኢትዮጵያ እግርኳስ ተጫዋቾች ፕሬዚዳንት ኤፍሬም ወንድወሰን እና የሴት እግር ኳስ ተጫዋቾች ማኅበር ፕሬዚዳንት ቱቱ በላይን በዚህ የምክክር መድረክ ላይ እንዲገኙ ጥሪ ያደረገላቸው ሲሆን ሁለቱም ዛሬ ወደ ስፍራው ያቀናሉ።

መርሐግብሩ በዚህ መልኩ ይካሄዳል
ነገ November 7 ( ጥቅምት 28 ) የእንኳን ደኅና መጣችሁ እና የመርሐግብር መክፍቻ ፣ November 8 ( ጥቅምት 29) ውይይት እና ኮርያ ሪፐብሊክ ከ ኔዘርላንድስ የሚያደርጉትን የሴቶች ከ17 ዓመት በታች የዓለም ዋንጫ የፍጻሜ ጨዋታን ከታደሙ በኋላ በነጋታው ወደየ ሀገራቸው የሚመለሱ ይሆናል።

