👉 “እነዚን ልጆች ላይ ‘Invest’ አድርገን በተዘጋጀነው ልክ ዋናው ብሔራዊ ቡድን ላይ ‘Invest’ አድርገን አናውቅም”
👉 “ዕቅዳችን ለአፍሪካ ዋንጫ ማለፍ የሚችል ቡድን ገንብተናልና ማለፍ አለብን …”
👉 “ውድድሩ የሚድያ ሽፋን እንዲያገኝም ከአዲስ ቴሌቪዥን እና ከድሬ ቴሌቪዥን ጋር እየተነጋገርን ነው”
ቀደም ብለን ሀገራችን በምታስተናግደው የሴካፋ ዞን ከ17 ዓመት በታች አፍሪካ ዋንጫ የማጣርያ ውድድር ዙርያ በኢፌድሬ ባህልና ስፖርት፡ የስፖርት ዘርፍ ሚኒስተር ድኤታ አቶ መኪዩ መሐመድ የሰጡትን ሀሳብ ማቅረባች ይታወሳል፤ አሁን ደግሞ
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳይያስ ጅራ በመግለጫው ከሰጡት ኃሳብ ለአንባብያን በሚመች መልኩ አንኳር ነጥቡን አቅርበንላችኋል።
“ታግዶ የነበረው አበበ ቢቂላ ስቴድየም እና ለሴቶች ለአንድ ጨዋታ ብቻ ተፈቅዶ የነበረውን የድሬዳዋ ስቴድየም ለማስፈቀድ ከካፍ ጋር ከፍተኛ የሆነ ስራ ነው ስንሰራ የቆየነው በፌደሬሽን፤ በስተመጨረሻ ድሬዳዋ እና አበበ ቢቂላ ስቴድየሞች ዳግም ለዚህ ውድድር እንዲፈቀዱ ተደርጓል። ለውድድሩ ጥሩ ዝግጅት እያደረግን እንገኛለን። ውድድሩ የሚድያ ሽፋን እንዲያገኝም ከአዲስ ቴሌቪዥን እና ከድሬ ቴሌቪዥን ጋር እየተነጋገርን ነው ያለነው፤ ሲጠናቀቅ የምናሳውቅ ይሆናል”።

“እነዚን ልጆች ላይ ‘Invest’ አድርገን የተዘጋጀነው ልክ ዋናው ብሔራዊ ቡድን ላይ ‘Invest’ አድርገን አናውቅም። ከፍተኛ ወጪ አውጥትተናል ወጪው ብቻም ሳይሆን ስራው ራሱ እጅግ የተጠና በቴክኖሎጂ የታገዘ፤ እያንዳንድ ልምምድ ሲሰሩም በጨዋታም እንደ ቡድን ቡድኑ ምን እንደሚመስል እንደ ግል ደግሞ ግለ-ሰቦቹ ምን እንደሚመስሉ እነ አቶ አምሳሉ ጥላሁን እና ሾን ብሌክማን ይዘውት በመጡት ማሽን እየታገዙ ነው እየታዩ የነበሩት። ባለ ሞያ በሁሉም ዘርፍ የተሟላለት፤ እዚህ ቀረ የማይባል በሁሉም ዘርፍ የተሟላለት ነው ብሎ መውሰድ ይቻላል”።
“ተስፋ ይሰጣል ትክክኛውም የእድገት መንገዱ ይሄን ሊሆን ይችላል የሚልም የሚያሳይ ዝግጅት ነው ስናደርግ የነበረው። በርግጥ በጀቱ ከፍተኛ መሆኑ መታወቅ ያለበት። ጥሩ ዝግጅት አድርገና ግብ አስቀምጠን ነው የተነሳነው፤ ይሄ ቡድን ለአፍሪካ ዋንጫ ማለፍ አለበት። ተያይዘን ማለፍ አለብን ቡድኑም ብቻ ሳይሆን እኛም ሁሉም ባለሞያ ጋር ያለው ዕቅድ ይሄ ነው። ዕቅዳችን ለአፍሪካ ዋንጫ ማለፍ የሚችል ቡድን ገንብተናልና ማለፍ አለብን ነው፤ ብለን ይሄን ኃላፊነት ሰጥተናቸው ነው እነ ቤን እና አምሳሉ እየተንቀሳቀሱ ያሉት። ከፍተኛ ትኩረት ነው የሰጠነው፤ እግዚአብሔር ደግሞ ረድቶን በልጆቹ ጥረት እናልፋለን ብዬ አስባለሁ”።


