በአሠልጣኝ ሙሉጌታ ምሕረት የሚመራው መቻል አይቮሪኮስታዊ የመሐል ተከላካይ አስፈርሟል።
በክረምቱ የዝውውር መስኮት ከአሠልጣኝ ቡድን አባላት ጀምሮ በርከት ያሉ ለውጦችን ያደረገው መቻል ስምንት ሳምንታትን ባስቆጠረው የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 15 ነጥቦችን ሰብስቦ ሦስተኛ ደረጃ ላይ መቀመጡ ይታወቃል። በሊጉ ጥቂት ግቦችን በማስተናገድ 8ኛ ደረጃ ላይ ከባህር ዳር ከተማ፣ ሸገር ከተማ እና ኢትዮጵያ መድን ጋር በመስተካከል (6 ግቦች) የተቀመጠው ጦሩ የኋላ መስመሩን ለማጠናከር ከክለብ ነፃ የሆኑ የውጪ ሀገር ተጫዋቾችን ሲፈልግ ቆይቶ በዛሬው ዕለት በቦታው ተጫዋች ማስፈረሙን ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች።

ተጫዋቹ ታውላ ቴዎፊል ኡራ ነው። በአሴስ ሚሞሳስ ቆይታ ያደረገው 1:96 የሚረዝመው የመሐል ተከላካዩ ኡራ ከትናንት በስትያ ወደ አዲስ አበባ የመጣ ሲሆን በትናንትናው ዕለት የህክምና ምርመራውን አድርጎ ከደቂቃዎች በፊት ለአንድ ዓመት በመቻል ቤት የሚያቆየውን ስምምነት ፈፅሟል።


