የዓምናው የሊጉ አሸናፊ ኢትዮጵያ መድን ከአማካዩ ጋር መለያየቱ ታውቋል።

ከባለፈው ዓመት ከነበረው ጠንካራ ስብስባቸው በርከት ያሉ ተጫዋቾችን ያጡት እና በዘንድሮ የውድድር ዓመት ካደረጓቸው አስራ ዘጠኝ ጨዋታዎች ሃያ ነጥብ በመሰብሰብ ከወራጅ ቀጠናው በአንድ ደረጃ ከፍ ብለው አስራ ስድስተኛ በመሆን አንደኛ ዙርን ያጠናቀቁት ኢትዮጵያ መድኖች ባለፉት ሁለት ዓመታት በሀዋሳ ከተማ ቆይታ ከነበረው እና የያዝነውን ግማሽ ዓመት አብሯቸው ከቆየው ጋናዊ አማካይ ሚሼል ኦቱሉ ጋር መለያየታቸውን አውቀናል።
ከዚህ ቀደም በግሬት ኦሎምፒክስ፣ ፓርቹጋል አምርቶ ፓርቲሞኔንሴ እንዲሁም ለሌጎን ሲቲ መጫወት የቻለው ሚሼል ከስድስት ወር የኢትዮጵያ መድን ቆይታ በኋላ በስምምነት መለያየቱ ታውቋል።

