በሲዳማ ቡና ቆይታ የነበረው የመስመር ተጫዋች ከቡድኑ ጋር በስምምነት ተለያይቶ ወደ ሌላ ክለብ ለማምራት ከስምምነት ደርሷል

ባለፈው ዓመት መጀመሪያ መቻልን ለቆ በሁለት ዓመታት ውል ወደ ሲዳማ ቡና በማምራት ከቡናማዎቹ ጋር ቆይታ የነበረው የመስመር ተጫዋቹ ሳሙኤል ሳሊሶ ከሲዳማ ቡና ጋር ያለውን ቀሪ ውል በስምምነት አፍርሶ ወደ ኢትዮጵያ መድን ለመቀላቀል ከስምምነት ደርሷል። በ2007 ሼር ኢትዮጵያን ለቆ ወደ መቻል ካመራ በኋላ በጦሩ ቤት አራት የውድድር ዓመታት ያሳለፈው ተጫዋቹ ቀጥሎ በመቐለ 70 እንደርታ፣ በወልቂጤ ከተማ፣ ሰበታ ከተማ እንዲሁም በመቻል እና ሲዳማ ቡና መጫወቱ የሚታወስ ሲሆን አሁን ደግሞ በ2011 አብረው የሊጉን ዋንጫ ካሳኩት አሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ ጋር ለመስራት ወደ ኢትዮጵያ መድን ለማምራት ከስምምነት ደርሷል።
ኢትዮጵያ መድን ዛሬ ባደረገው የአቋም መፈተሻ ጨዋታ የተሳተፈው ተጫዋቹ በቀጣይ ቀናት በይፋ ፌርማውን ያኖራል ተብሎም ይጠበቃል።

