ዋልያዎቹ ከትናንቱ ድል መልስ ልምምድ ሰርተዋል

ዋልያዎቹ ከትናንቱ ድል መልስ ልምምድ ሰርተዋል

በአሰልጣኝ ዮሐንስ ሳሀሌ የሚመሩት ዋልያዎቹ ከትናንትናው ጨዋታ በኋላ ያደረጉትን ልምምድ አስመልክቶ የተጠናከረ ዘገባ እነሆ!

በኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ጥረት የፊፋን ካላንደር መሰረት ያደረገ ዓለም አቀፍ ሁለት የወዳጅነት ጨዋታ ከማላዊ አቻው ጋር ለማድረግ በታሰበው መሠረት ትናንት በድሬደዋ ዓለም አቀፍ ስታዲየም የመጀመርያ ጨዋታቸውን ያደረጉት ዋልያዎቹ ፍፁም ጥላሁን በመጀመርያው ደቂቃ ባስቆጠረው ብቸኛ ጎል 1-0 ማሸነፋችን ይታወሳል።

ዛሬ አመሻሽ ላይ ከትናንቱ ጨዋታ መልስ ለሚዲያ በተፈቀደው አስራ አምስት ደቂቃ የዋልያዎቹ ምሽት አስራ ሁለት ሰዓት ላይ በድሬደዋ ስተዲየም ሠርተዋል።

– ሶከር ኢትዮጵያ በነራት የብሔራዊ ቡድኑ አስራ አምስት ደቂቃ ምልከታ ላይ ቡድኑ በህብረት ሆነው ግማሽ ሜዳ በመሮት ሰውነታቸውን ካማማቁ በኋላ ቡድኑ ለሁለት ተከፍሎ ልምምዱን እንዲሰራ ሲያደርግ አስተውለናል

– በትናንቱ ጨዋታ ሙሉ ዘጠና ደቂቃ እና አብዛኛውን የጨዋታ ክፍለ ጊዜ የሸፈኑት ግብጠባቂ አቡበከር ኑራ፣ ራምኬል ጀምስ፣ ቸርነት ጉግሳ ፣ ፍፁም ጥላሁን፣ ሳሙኤል ዮሐንስ፣ ሀብታሙ ተከስተ፣ ቢንያም በላይ እና ዳዋ ሆቴሳ የተጫወቱት የማገገምያ (Recovery Training ) ስራ ሰርተዋል

– የተቀሩት የቡድኑ አባላት ማለትም ያልተጫወቱት እና ተቀይረው ወደ ሜዳ የገቡት የኮንዲሽኒንግ (conditioning ) ስራ ሲሰሩ ተመልክተናል

– የቡድኑ የኋላ ደጀን የሆነው አንበሉ ያሬድ ባዬ ከቡድኑ ጋር አብሮ ካማሟቀ በኋላ ለብቻው ተነጥሎ የእግሩ ጡንቻዎች ላይ የፊዝዬቴራፒ አገልግሎት በህክምናው ባለሙያ ብሩክ ደበበ ሲደረግለት ነበር

– በዛሬው ልምምድ ሁሉም የቡድኑ አባላት የተገኙ ሲሆን በመልካም ጤንነት ላይ እንደሚገኙ ለመመልከት ችለናል።

– ዋልያዎቹ ነገ የመጨረሻ ልምምዳቸውን ከሰሩ በኋላ ሁለተኛ ጨዋታቸውን ማክሰኞ በድሬደዋ ዓለም አቀፍ ስታዲየም ምሽት 12:00 ጨዋታቸውን የሚያደርጉ ይሆናል።

ሶከር ኢትዮጵያም እንደተለመደው ከስፍራው በመሆን የብሔራዊ ቡድኑ ኩነቶችን እየተከታተለች ወደ እናተ የምታደርስ ይሆናል።