በአሰልጣኝ ኢያሱ መርሐጽድቅ (ዶ/ር) የሚሰለጥኑት ሸገር ከተማዎች ሦስት ተጫዋቾችን ማስፈረማቸው ታውቋል

አስቀድመው የፉአድ አብደላ ፣ ብሩክ ባይሳ፣ መለሰ ሚሻሞ ፣ ሀብታሙ ታደሰ እና አብነት ደምሴን ወደ ስብስባቸው በመቀላቅ ቡድኑን እያጠናከሩ የሚገኙት ሸገሮች አሁን ደገወሞ ሦስት ተጫዋቾችን ማስፈረማቸውን አውቀናል።
የመጀመሪያው ፈራሚ በአንደኛ ሊግ ድንቅ ብቃቱን ያሳየው አጥቂው ኡመድ ኡፒት ነው፤ አጥቂው በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በፉሪ ክፍለ ከተማ አሳልፎ የነበረ ሲሆን አሁን ደግሞ ለሸገር ከተማ ለሁለት ዓመት ለመጫወት ፊርማውን አኑሯል።
ሌላኛው ሸገር ከተማን የተቀላቀለው አጥቂው እንዳልካቸው ታደለ ነው። በአንደኛው ሊግ ከቡታጅራ ከተማ ጋር ጥሩ ጊዜ ያሳለፈ እና ወደ ፊት ተስፋ የሚጠላበት ተጫዋቹ ሸገር ከተማን ለሁለት ዓመታት ለመጫወት ተስማምቷል።
ሥስተኛው ለሸገር ከተማ የፈረመው ተከላካዩ እዩኤል አበባየሁ ነው። በከፍተኛ ሊግ ከየካ ክፍለ ከተማ ጋር ያሳለፈው ተከላካዩ ከኋላ እየመጣ ጎሎችን በማስቆጠር ጥሩ ግልጋሎት ሲያሳይ ቆይቶ አሁን ማረፊያው ሸገር ከተማ ሆኗል።

