ሻምፒዮኞቹ የአህጉራዊ ውድድር ጨዋታቸውን መቼ እና የት ያደርጋሉ ?

ሻምፒዮኞቹ የአህጉራዊ ውድድር ጨዋታቸውን መቼ እና የት ያደርጋሉ ?

በካፍ ቻምፒየንስ ሊግ ሀገራችንን የሚወክለው የወቅቱ የሊጉ ሻምፒዮን ሲዳማ ቡና በአህጉራዊው ውድድር የቅድመ ማጣሪያ የደርሶ መልስ ጨዋታዎቹን የት እና መቼ እንደሚያደርግ አጣርተናል።

በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ የኢትዮጵያን ትልቁን የሊግ እርከን ውድድር ያሸነፈው ሲዳማ ቡና የሀገሪቱ አሸናፊ መሆኑን ተከትሎ ኢትዮጵያን በአህጉራዊ ትልቁ የክለቦች መድረክ እንደሚወክል ይታወቃል። በአሠልጣኝ ያሬድ ገመቹ የሚመራው ቡድኑ ስብስቡን እያጠናከረ ዝግጅቱን የጀመረ ሲሆን ከቻዱ ኤግሎንስ ክለብ ጋር ያለው የደርሶ መልስ ጨዋታ የት እና መቼ እንደሚያደርግ ሶከር ኢትዮጵያ መረጃ ሰብስባለች።

የመጀመሪያ ጨዋታውን ከሜዳው ውጪ የሚያደርገው ሲዳማ ቡና ቅዳሜ ነሐሴ 30 30 ሺ ተመልካቾች መያዝ በሚችለው በቻዱ ስታድ ኦሊምፒክ ማርቻል ኢድሪስ ዴቢ ኢቶ የሚያከናውን ሲሆን የመልስ ጨዋታውን ደግሞ እሁድ መስከረም 3 በድሬዳዋ ስታዲየም የሚያከናውን ይሆናል።