የአጥቂው ጉዳይ …. ?

የአጥቂው ጉዳይ …. ?


እዮብ አለማየሁ ለሁለት ክለቦች የፈረመ ሌላኛው ተጫዋች በመሆን ውዝግብ ፈጥሯል።

ከሳምንታት በፊት አጥቂው እዮብ አለማየሁ የወልዋሎ የክረምቱ የመጀመሪያ ፈራሚ ለመሆን ከስምምነት እንደደረሰ መግለፃችን ይታወሳል ፤ ተጫዋቹ ሐምሌ 30 ወልዋሎን ለመቀላቀል ተስማምቶ የቅድመ ስምምነት እንደፈረመ የዝግጅት ክፍላችን ማስረጃዎችን ያገኘች ሲሆን ተጫዋቹ ግን ከቀናት በኋላ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ለመቀላቀል መስማማቱን ሰምተን መረጃ አጋርተናችሁ ነበር። ድረ ገፃችን ባደረገችው ማጣራት ተጫዋቹ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክም ቤት የቅድመ ስምምነት ፌርማውን አኑሯል። ይህንን ተከትሎም በክረምቱ ለሁለት ክለቦች የፈረመ ሌላኛው ተጫዋች ሆኗል።

ተጫዋቹ የመጀመሪያ የቅድመ ስምምነት ፊርማውን ያኖረላቸው ወልዋሎዎች ከአጥቂው ጋር የቅድመ ስምምነት እንደፈፀሙ በመግለፅ ለፌደሬሽኑ ደብዳቤ ማስገባታቸውም ታውቋል።