ጋሞ ጨንቻዎች የመጨረሻ ፈራሚያቸውን አግኝተዋል

ጋሞ ጨንቻዎች የመጨረሻ ፈራሚያቸውን አግኝተዋል

አዲስ አዳጊዎቹ  ሁለት ተጫዋቾችን በማስፈረም ዝውውራቸውን አጠናቀዋል።

በዋና አሰልጣኛቸው ማቲዮስ ለማ እየተመሩ ወደ ወደ ሊጉ ካደጉበት ጊዜ ጀምሮ ቡድናቸውን ለማጠናከር የዝውውር ስራዎችን በመስራት ቅድመ ዝግጅታቸውን ሲያደረጉ ቆይተው አሁን የመጀመርያ ጨዋታቸውን በሜዳቸው ኢትዮጵያ መድንን ለመግጠም እየተጠባበቁ የሚገኙት ጋሞ ጨንቻዎች ሁለት ተጫዋቾችን በማስፈረም ዝውውራቸውን አጠናቀዋል።

የመጀመርያው ፈራሚ ባለ ብዙ ልምዱ አማካይ ሙሉዓለም መስፍን ሲሆን ከዚህ ቀደም በአርባምንጭ ከተማ፣ ሲዳማ ቡና ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ ፣ ምድረ ገነት ሽረ እና በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት የኢትዮጵያ ዋንጫን ከወልዋሎ ጋር በማንሳት ጥሩ ጊዜ ያሳለፈ ሲሆን አሁን ወደ አዲስ አዳጊዎቹ ጋሞ ጨንቻ መዳረሻውን አድርጓል።

ሌላኛው ፈራሚ ሁለገቡ ተጫዋች ፀጋዬ አበራ ነው። መነሻውን አርባምንጭ ከተማ በማድረግ ከታዳጊ እስከ ዋናው ቡድን መጫወት የቻለ ሲሆን በመቀጠል በባህር ዳር ከተማ አሳልፎ በድጋሚ ወደ አርባምንጭ ተመልሶ የተጫወተ ሲሆን አሁን ዳግም ለትውልድ ሀገሩ ጋሞ ጨንቻ ለመጫወት ፊርማውን አኑሯል።