በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 10ኛ ሳምንት ፈረሰኞቹ በተከታታይ 3ኛ ጨዋታቸውን አሸንፈው 2ኛ ደረጃን ከመከላከያ ተረክበዋል፡፡ የሶከር ኢትዮጵያው ሚልኪያስ አበራ ጨዋታውን ተመልክቶ የሚከተለውን ታክቲካዊ ትንታኔ አዘጋጅቷል፡፡
የአሰልጣኝ ዶ ሳንቶሱ ቅዱስ ጊዮርጊስ በመጀመርያው አጋማሽ እና በሁለተኛው አጋማሽ የመጀመርያዎቹ 15 ደቂቃዎች ወደ 4-1-3-2 ያመዘነ 4-4-2ን ተግባራዊ አድርገዋል፡፡ ፈረሰኞቹ በመጨረሻዎቹ 20 እና 25 ደቂቃዎች ለውጥ ምክንያት 4-3-3 የቀረበ የተጫዋች የሜዳ ላይ አደራደር መጠቀማቸው ልብ ይሏል፡፡ በአሰልጣኝ ሳምሶን አየለ የሚመራው እንግዳው ቡድን ዳሽን ቢራ ከአምናው ቻምፒዮን ቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ባደረገው ጨዋታ ሙሉ ጊዜውን 4-3-3 ፎርሜሽን ተጠቅሟል፡፡
ምስል 1
የመጀመርያው 45 ደቂቃ የጨዋታ ሒደት
በተደጋጋሚ እንደታየው የቅዱስ ጊዮርጊስ የግራ መስመር ሊነገርለት የሚገባ ጠንካራ ጎኑ ነው፡፡ ቡድኑ ማጥቃትን እና መከላከልን ሚዛናዊ በሆነ መልኩ የሚከውን ዘመናዊ የመስመር ተከላካይ አለው፡፡ (ዘካርያስ ቱጂ) የዳሽኑ አሰልጣኝ በጨዋታ ሒደት እየጎመራ የሚመጣውን የዘካርያስ እንቅስቃሴ ለመግታት ያስችላቻው ዘንድ የመጀመርያ ተከላካዩ ፊት በመቆም እንቅስቃሴውን በተለይም የፊት ለፊት የማጥቃት እንቅስቃሴ የሚከናወንበትን (overlapping movement) ለመገደብ ከማጥቃት ይልቅ በመከላከሉ ረገድ ጉልህ ድርሻ ያለውን ዮነታን ከበደ ወደ ቀኝ አምጥተው የተሻ ግዛውን ወደ ግራ ወስደውታል፡፡ ይህ ውሳኔያቸው በመጀመርያ አካባቢ ሰርቶላቸው ነበር፡፡ ዮናታን በመጠኑ የዘካርያስን እንቅስቃሴ ለማፈን (stifle ለማድረግ ) ችሏል፡፡ ነገር ግን ወጣቱ ፉልባክ ራሱን ከተጋጣሚ አማካይ ተጭኖ የመጫወት ዘዴ (Pressing System) አላቆ ከማን ማርኪንግ ወጥመድ የሚያመልጥበትን መንገድ መፈለግ አልተሳነውም፡፡ ለራሱ ተከላካዮች ቀርቦ ማርክ ያደረገውን (Press ያደረገውን) ዮናታን ከበደ ርቆ የማሰብያና ኳስን መቀባበያ ጊዜ ያስገኘበት መንገድ ሙገሳ የሚቸረው ነው፡፡ በዚህ ሒደት በመስመሩ የተሰለፈው የቡድን አጋሩ በኃይሉ አሰፋ የታክቲክ ግንዛቤና ሚዛናዊ እንቅስቃሴ አይነተኛ አስተዋፅኦ አበርክቷል፡፡ ለዘካርያስ የፊት ለፊት ፈጣን እንቅስቃሴ የሚያደርገው ከኳስ ውጪ እንቅስቃሴ (Off the Ball) ለፉልባኩ ሰፊ ክፍተት የሚፈጥርለት ነበር፡፡ ቡድኑ ጨዋታውን በአሸናፊነት ያጠናቀቀበትን ግብ ያስገኘበት መንገድ ከዚሁ የመሰመር አማካይ (በኃይሉ) መሆኑ ይህንን የቡድኑን ጠንካራ ጎን አጉልቶ የሚያሳይ ነው፡፡ ከግራ መስመር የተመሰረተውን ኳስe በሚገርም መጣመር በኃይሉ እና ዘካርያስ አንድ ሁለት ተቀባብለው ፤ በኃይሉ ወደ መስመሩ ሲወጣ ዘካርየስ ደግሞ ኳሱን ይዞ ወደመሃል በመግባት (Underlapping movement) ተመልሶ በኃይሉ ከማእዘን መምቻው አካባቢ ወደ ግብ ያጠፋትን ኳስ ዳዋ ሁቴሳ ከመረብ አሳርፏታል፡፡
ዳሽኖች በአማካያቸው አስራት መገርሳ አማካኝነት ወደ ግብ የሚልካቸው ረጃጅም ኳሶች እና ቅብብሎች ልኬታቸውን የተበቁ ቢሆኑም በተጋጣሚያቸው ተቀራርቦ የመከላከል ስልት በቀላሉ ሲከሽፈፍ ታይቷል፡፡ በ31ኛው ደቂቃ አካባቢ ከግራ መስመር የተሸ ግዛው ያሻማው (Diagonal Pass) ረጅም ኳስ በጅለሎ ሻፊ በግንባር ጥሩ ሙከራ ተደርጎበታል፡፡ ይህንን ኳስ አስራት ቢጠቀምበት ኖሮ ከነበረበት ቦታ አንፃር የተሸለ ይሆን ነበር የሚል ግምት አለኝ፡፡ ጊዮርጊሶች የግራ መስመራቸውን ለማጥቃት አጨዋወታቸው የመረጡ ሲሆን ተጋጣሚያቸው ደግሞ የቀኝ መስመሩ በተለይም አንዳረርጋቸውን በቁጥር የመስመር ብልጫ በመውሰድ (Overload በማድረግ) የማጥቃት እንቅስቃሴያቸውን (attacking Phase ) ያካሂዱ ነበር፡፡ በዚህ ምክንያት በዛ መስመር አሉላ ለተደጋጋሚ ጊዜ ጥፈት እንዲፈፅም አስገድዶት ውሏል፡፡ በ43ኛው ደቂቃ ላይም የዳሽኑ ዳዊት ሞገስ ከቆመ ኳስ (አሉላ በሰራው ጥፋት የተገኘ ) ጥሩ የግብ ሙከራ አድርጓል፡፡ በዚህም ለእረፍት በቅዱሰ ጊዮርጊስ 1—0 መሪነት ወጥተዋል፡፡
ምስል 2
ሁለተኛው አጋማሽ
ይህኛው ክፍለ ጊዜ ጊዮርጊሶች የተወሰደባቸውን የመሃል ሜዳ የቁጥር ብልጫ ለማካካስቸ መጠነኛ ለውጥ ያደረጉበት ነው፡፡ የተከላካይ ክፍሉም ይበልጥ ወደፊት ተጠግቶ በመጫወቱ ከአማካይ ክፍሉ ተነጥሎ ይታይ የነበረው ተስፋዬ አለባቸውም በተሸለ የማጥቃት አጨዋወት ላይ ተሳታፊ መሆን ቻለ፡፡ ቢሆንም ቡድኑ ከተጋጣሚው ቡድን (ዳሽን ቢራ) ቀኝ መስመር የሚሻገሩ ረጃጅም ኳሶችን የመከላከል ድክመት ነበረበት፡፡ በ(Far Post) የመከላከል ብቃትም አናሳ ነበር፡፡ ተከላካዮች የተጋጣሚን ኳስን ያማከለ እንቅስቃሴ (Ball oriented movement) በመመልከት ያደረጉት የመከላከል አቀራረብ በኋላኛው ቋሚ የሚኖራቸው ቦታ ክፍት ሲየደርጉት ተስተውሏል፡፡
ዳሽኖች የመስመር ተከላዮቻቸውን ይበልጥ በማጥቃት አጨዋወት ላይ ተሳተፊ ቢደርጋቸውም በተለይ በግራ መስመር ዳዊት ኦቨር ላፕ አድርጎ ቶሎ ስለማይመለስ መስመሩ ለአደጋ ሲጋለጥ ታይቷል፡:፡ ቡድኑ ብዙ ኳሶችን መቀባበል ቢችልም ወደ የግብ ክልል የሚላኩ ኳሶች መድረሻቸውን ያልጠበቁና የተዛነፉ ነበሩ፡፡
የጊዮርጊስ አጥቂዎች (ፍፁም እና ዳዋ) በመካከላቸው ያለውን ርቀት በማስፋት በተደጋጋሚ ኳላቸው ለሚገኘው ምንተስኖት የመጫወቻ ክፍተት (space) ሲፈጥሩ ተስተውሏል፡፡ በተጨማሪም በተጋጣሚያቸው የመሃልና የመMስመር ተከላካዮች መካከል (Channels) የሚያደርጉት እንቅስቀሴም የመቀባበያ አማራጭን እንዲፈጥሩ አስችሏቸዋል፡፡
ፈረሰኞቹ ከመከላከል ወደማጥቃት በሚሚረገው ሽግግር ላይ ፍጥነት አንሷቸው ታይቷል፡፡ በተለይ ተስፋዬ በዚህ ሒደት ኳስን ሲያዘገይ ታይቷል፡፡ ምናልባት በbላይኛው የሜዳ ክፍል ያለ የቡድን አጋሮቹ በሽግግር ወቅት (ትራንዚሽን ፌዝ) ቋሚ ቦታቸው ላይ ያለመገኘታቸው ችግርም አንዱ ሊሆን እንደሚችል ይገመታል፡፡
ሳይጠቀስ መታለፍ የሌለበት ሌላው የቡድኑ ጠንካራ ጎን ተከላካዮቹ ሳላዲን እና አይዛክ የመስመር ተከላካዮዮን የማገዝ ሐሒት ነው፡፡ ዘካርያስ እና አንዳርጋቸው ለማጥቃት ወደ ፊት በሚሔዱበት ጊዜ ሳላዲን ወደ መስመር በመለጠጥ ተጋጣሚ ፈጣን የሆነ የመስመር መልሶ ማጥቃት (Flank transition) አጨዋወትን የሚከላከሉበት መንገድ ሊያስመሰግናቸው የሚገባ ነው፡፡
ምስል 3