ኢትዮጵያዊው አጥቂ ፍቅሩ ተፈራ በደቡብ አፍሪካው ቤድቬስት ዊትስ ክለብ ውስጥ ልምምድ እየሰራ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡ ፍቅሩ ያለፉትን ወራት በህንድ ሂሮ ሱፐር ሊግ ቻምፒዮን ለሆነው አትሌቲኮ ካልካታ የተጫወተ ሲሆን ፤ ለክለቡም በ12 ጨዋታ 5 ግቦችን አስቆጥሯል እንዲሁም 5 ለግብ የሚሆኑ ካሷችን አቀብሏል፡፡ ፍቅሩ በሂሮ ሱፐር ሊግ ፍፃሜ ጨዋታ በጉዳት ምክንያት መሰለፍ አልቻለም ነበር፡፡
ከምዕራብ ቤንጋሉ ክለብ ጋር የአጭር ጊዜ ውል የነበረው ፍቅሩ አሁን በደቡብ አፍሪካው ቤድቬስት ዊትስ ውስጥ ልምምድ እየሰራ ይገኛል፡፡ አዲሱ የህንድ ሱፐር ሊግ የሚጀመረው በመጪው መስከረም በመሆኑ አብዛኞቹ ክለቦች ተጫዋቾቻቸውን ወደ ሌላ ሀገር ሄደው የሚጫወቱበትን ሁኔታ አመቻችተዋል፡፡ ባሰለፍነው ሰኞ ከዊትስ ጋር ልምምድ የሰራው ፍቅሩ እራሱን ብቁ ለማድረግ እንጂ ለዊትስ ሊፈርም እንዳልሆነ ታውቋል፡፡
የዊትስ ክለበ ዋና ስራ አስኪያጅ ጆዜ ፌሬራ በጉዳዩ ላይ በሰጡት አስተያየት “ፍቅሩ ልምምድ ብቻ እየሰራ ነው፡፡ ጋቭን ሃንትን (ቤድቬስት ዊትስ ዋና አሰልጣኝ ) ልምምድ ለመስራት ፍቃድ ጠይቆ እሽታን በማግኘቱ ነው አሁን ልምምድ እየሰራ የሚገኘው፡፡” ብለዋል፡፡ ፍቅሩ እና ጋቭን ከዚህ በፊት በሱፐር ስፖርት ዩናይትድ በሁለት የተለያዩ ጊዜያት አብረው ሰርተዋል፡፡