የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌድሬሽን አዲስ የሉሲ አሰልጣኝ ቀጠረ

 

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌድሬሽን አዲስ የኢትዮጵያ ሴቶች ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ ቀጥሯል፡፡ ፌድሬሽኑ የሲዳማ ቡና የሴት ቡድን አሰልጣኝ የሆነቸውን በኅይሏ ዘለቀን ዋና አሰልጣኝ አድርጎ መሾሙ ተነግሯል፡፡ የቅዱስ ጊዮርጊስ ሴት ቡድን አሰልጣኝ ሰላም ዘርዓይ ደግሞ ምክትል ሆና ሉሲዎችን የምታገለግል ይሆናል፡፡ የኢትዮጵያ ሴቶች ብሄራዊ ቡድን ላለፉት ረጅም ወራት ያለ ቋሚ አሰልጣኝ ቆይቷል፡፡ አሰልጣኝ ስዩም ከበደ ወደ የመን ካቀኑ በኅላ ቡድኑን ምክትላቸው የነበረው የንግድ ባንኩ ብርሀኑ ግዛው ሊረከቡ ይችላል ተብሎ በከፍተኛ ሁኔታ ተጠብቆ ነበር፡፡ ነገር ግን በኅይሏ ዘለቀ የፌድሬሽኑ ምርጫ ሁናለች፡፡ የሁለቱ አሰልጣኞች ምርጫ ቅሬታ ፈጥሯል፡፡ አንዳንድ በምርጫው የተሳተፉ አሰልጣኞች የፌድሬሽኑ መስፈርት ግራ እንዳጋባቸው እና ግልፅነት የጎደለው መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ ለሉሲ ዋና አሰልጣኝነት የቀድሞ የኢትዮጵያ ቡና አሰልጣኝ ጳውሎስ ማንጎ ውድድር ውስጥ ከነበሩት አሰልጣኞች ውስጥ የሚጠቀስ ነው፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *